ጀነራል ሞሃመድ ዳጋሎ ኤርትራ የሱዳንን ጦር ትረዳለች ሲሉ ከሰሱ።

ኢትዮ ሞኒተር፡12/02/2018፡- የሱዳን ፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሐይል መሪ ሌተናል ጀነራል መሀመድ ሀምዳን ዳጋል (ህመቲ) ኤርትራ ለሱዳን ጦር ተዋጊ ጄት እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እንደምትሰጥ ሲናገሩ ተደምጠዋል።
በተጨማሪም ኤርትራ በፖርት ሱዳን የኤርትራ ጦር ረዳት እና አዛዥ በመሆን ከአልፋሸር ኒያላ ኩርድፋን ጋር የሚደረገውን ጦርነት ትመራለች በማለት በግልጽ ከሰዋል።
መሐመድ ዳጋሎ በተመሳሳይ ሁኔታ ኤርትራን ከሶስት ወራት በፊት ጄኔራል አል-ቡርሃንን ትረዳለች በማለት ተናግሮ እንደነበር ይታወሳል።
መሐመድ ዳጋሎ ኤርትራ የሱዳንን ጦር እየረዳች ነው ሲሉ እሳቸው የሚመሩት ቡድን ደግሞ የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስን ጨምሮ የተለያዩ አገሮች እንደሚደግፈት የሱዳን ጦር ይከሳል።
በሌላ ዜና ዛሬ ጥቅምት 12 ቀን የሀገር ውስጥ በረራውን ሊጀምር የነበረው የካርቱም አየር መንገድ በሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት እንደደረሰበት ተገልፀዋል።
የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ሚያዝያ 2015 ከጀመረ ወዲህ የተቋረጠው የካርቱም አየር መንገድ የሱዳን ጦር ካረቱምን ከተቆጣጠረ በኋላ የመሰረተ ልማት ጥገና ሲደረግለት ቆይቷል። የሀገር ውስጥ በረራዎች ዛሬ እንደገና እንደሚጀምርም አስታውቆ ነበር።
ይሁን እንጂ አየር መንገዱ በታጣቂ ሃይሎች በሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ትላንት መመቱን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የጉዳቱ መጠን እና የበረራ አገልግሎቱ በታቀደለት ጊዜ ስለመደረጉ የተገለፀ ነገር የለም።