ዲፕሎማሲ

ኢትዮጵያ እና ሩስያ በኒዉክሌር ሐይል ትብብር ዙሪያ መወያየታቸው ተሰማ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ ወደ ሞስኮ በማቅናት፤ በኢኮኖሚ እና ኒውክሌር ትብብር ዙሪያ መከሯል፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 11/02/2018፡- የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ትናንት ጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ሞስኮ-ሩስያ መግባታቸው ተገለፅዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያመለክተው ዶ/ር ጌዲዎን ከሩስያ የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩ ማክሲሞ ሬሼንኮቭ ጋር ውይይት አድርገዋል።

ሁለቱ ወገኖች በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን አድማሰ ሰፊ እና የቆየ ትብብር የበለጠ ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል ተብሏል።

እንደ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ፣ የሩስያው የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ማክሲሞ ሬሼንኮቭ አገራቸው ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለምትደርገው ጥረት ሙሉ ድጋፍ እንደምትሰጥ ለዶ/ር ጌዲዎን አረጋግጠዋል።

እንዲሁም ዶ/ር ጌዲዎን ከሮሳቶም፣ ከሩስያ አቶሚክ ኤጄንሲ እና ሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለሥልጣናት ጋር በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የቴክኖሎጂ ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት አግባብ ተወያይተዋል።

በመስከረም ወር፣ ኢትዮጵያና ሩሲያ በኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል። ይህ ስምምነት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሞስኮ ባደረጉት ጉብኝት ወቅት ከተወያዩበት ሰፊ የትብብር አካል ነበር።

ስምምነቱ መስከረም 15 ቀን 2018 ዓ.ም በሩሲያ አቶሚክ ኢነርጂ ኮርፖሬሽን (ሮሳቶም) ዋና ዳይሬክተር አሌክሲ ሊካቼቭ እና በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) መካከል መፈረሙ ይታወሳል።

ይህም ሮሳቶም እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ለመገንባት ለሚያደርጉት ትብብር ተግባራዊ እርምጃን የሚያስቀምጥ መሆኑ ተገልጿል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates