ኢኮኖሚ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሳምንት 2 ጊዜ ወደ ሁመራ የበረራ አገልግሎት ሊጀምር እንደሆነ ተገለፀ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 11/02/2018፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኅዳር 10 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ዳግም ወደ ሁመራ የመንገደኞች የበረራ አገልግሎት ሊጀምር መሆኑን መስታወቁን የመንግስት ሚድያዎች ዘግበዋል፡፡
የበረራ አገልግሎቱ በሳምንት 2 ጊዜ እንደሚሆንም አየር መንገዱ አስታውቋል።
የሑመራ አየር መንገድ የሰሜኑ ጦርነት በ2013 ዓ/ም ከተጀመረ ጀምሮ እስካሁን መደበኛ የደንበኞች በረራ አገልግሎት ሰጥቶ አያውቅም፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሀገር ውስጥ በ23 ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ከ145 በላይ ወደሆኑ መደረሻዎች የበረራ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡