የተለያዩ
በድሬዳዋ ደወሌ የባቡር ጣቢያ በደረሰ አደጋ የ14 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 11/02/2018፡- መነሻውን ከደወሌ ባቡር ጣቢያ አድርጎ ወደ ድሬድዋ በመጓዝ ላይ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ባቡር ትላንት ሌሊት 8:00 አካባቢ በሶማሌ ክልል ሺኒሌ ወረዳ በደረሰበት አደጋ የ14 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል።
በአደጋው 29 ሠዎች ላይ ደግሞ ከከባድ እስከ ቀላል ጉዳት መድረሱን የሺኒሌ ወረዳ አስተዳደር ማስታወቁን የድሬዳዋ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በሺኒሌ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ በማግኘት ላይ ይገኛሉ የተባለ ሲሆን የአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሚገኝም ተዘግቧል።