የተለያዩ

የኬንያ ፖሊስ የቀድሞ ጠ/ሚ ራይላ ኦዲንጋን አስከሬን ለመሰናበት የተሰበሰቡ ሰዎች ላይ ተኩስ ከፍቶ ቢያንስ የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተሰማ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 07/02/2018፡- በኬንያ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋን አስከሬን ለመሰናበት በርካታ ሰዎች በተሰበሰቡበት ስታዲየም ፖሊስ ጥይት እና አስለቃሽ ጭስ በመተኮሱ ቢያንስ የሦስት ሰዎች ሕይወት መለፉን ተዘግቧል።

ታዋቂው የመብት ተሟጋች ድርጅት ቮካል አፍሪካ ለቢቢሲ እንደገለፀው በግርግሩ ከተገደሉት ሰዎች መካከል የሦስት ሰዎች አስከሬን ወደ ከተማዋ ዋና የሬሳ ማቆያ ክፍል ተወስዷል።

የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት ከሆነ ፖሊስ የተሰበሰቡትን ሐዘንተኞች ለመበተን በተኮሰው ጥይት ሌላ ተጨማሪ አንድ ሰው ሞቷል።

በዋና ከተማዋ ናይሮቢ በሚገኘው ስታዲየም በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ ፖሊሶች የተኮሱት ጥይት ዓይነት እስካሁን ግልፅ አይደለም።
ቮካል አፍሪካ ግን የሞቱት ሰዎች በጥይት መቁሰላቸውን አስታውቋል።

በኬንያ የፖለቲካ መድረክ ላይ ግዙፍ ስም እና ሰብዕና የነበራቸው ራይላ ኦዲንጋ በሕንድ ረቡዕ ዕለት ሕይወታቸው መለፉ ይታወሳል።
አስከሬናቸው ሐሙስ ጠዋት በአገሪቱ ዋና አውሮፕላን ማረፊያ የደረሰ ሲሆን ባለሥልጣናቱም በዚያ በተሰበሰበው ከፍተኛ ሕዝብ ምክንያት በረራዎችን ለአጭር ጊዜ ለማስቆም ተገድደዋል።

በአውሮፕላን ማረፊያው አካባቢ የተሰባሰቡ ሐዘንተኞች ወደ ተከለከሉ ስፍራዎች ጥሶ የገቡ ሲሆኑ በዚህም የተነሳ ለሁለት ሰዓታት ያህል “ለጥንቃቄ” በሚል በረራቸወዎች እንዲቋረጡ እና አየር ማረፊያው አንዲዘጋ ተደርጓል።

ከአየር መንገዱ ጀምሮ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች አስከሬኑን የያዘውን መኪና በማጀብ ከመሀል ከተማ በ10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው ስታዲየም በማጀብ በሰልፍ ተንቀሳቅሰዋል።

የራይላ ኦዲንጋን አስከሬን ለመሰናበት ከተጠበቀው ሕዝብ በላይ በመውጣቱ መጀመርያ ላይ በፓርላማው ሊካሄድ የነበረው የሽኝት ፕሮግራም ወደ ካሳራኒ ስታዲየም እንዲዞር ተደርጓል።

የኦዲንጋን አስከሬን ያዘው መኪና በሕዝብ በተጨናነቀው ስታዲየሙ ሲደርስ በርካታ ሰዎች ከውጭ ሆነው እየጠበቁ ነበር።
ከደቂቃዎች በኋላ ብዙ ሕዝብ የስታዲየሙን በር ጥሶ በመግባቱ ፖሊሶች አስለቃሽ ጭስ መተከሱና ለመሸሽ በተደረገው ጭንቅንቅ ሰዎች መሞታቸው ዘገባዎች አመልክቷል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates