የሱዳንን ሰላም ለማስቀጠል የአሜሪካ እና የሳዑዲ ባለስልጣናት በካይሮ እና ሮም መወያየታቸው ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 07/02/2018፡- የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር አብደል ፋታህ አል ቡርሃን ወደ ካይሮ ከጎበኙ ከ 24 ሰአታት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የአፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ማሳድ ቦሎስ ከግብፅመሪዎች የተወያዩ ሲሆኑ በመቀጠልም ከቻድ ፕሬዝዳንት እና ከሳውዲ አረቢያ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋሊድ ኤል ኬሪጂ ጋር በሱዳን ያለውን ግጭት ለማስቆም በሮም ተወያይተዋል።
ቦሎስ ከግብፁ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ከተወያዩ በኃላ ከቻድ ፕሬዝዳንት ማሃማት ኢድሪስ ዴቢ ጋር ተገናኝተዋል።
እነዚህ ዲፕሎማሲያዊ እርምጃዎች አሜሪካ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ግብፅ እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ያቀፈውን የኳድ ቡድን ዋሽንግተን ውስጥ በሱዳን ግጭት ለመፍታት ከአምስት ሳምንታት በኋላ ፍኖተ ካርታ ካቀረበ በኋላ የተደረገ እንደሆነ ሲዳን ትሪቡን ዘግቧል።
በአራቱ አገሮች የቀረበውን የሰላም ዕቅድ ጄነራል አልቡርሃን እንደማይቀበሉት መግለፃቸው ይታወሳል።
ቦሎስ ከሳዑዲ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋሊድ ኤል-ኬሬጂ ጋር ግጭቶችን ለመፍታት እና በአካባቢው ሰላምን ለማስፈን የጋራ ጥረቶችን ለማጠናከር መወያየታቸውን ተገልጸዋል።
“ሱዳንን በተመለከተ ሰላምና መረጋጋትን ለመመለስ እና የሱዳንን ህዝብ ስቃይ ለማስቆም አስቸኳይ እና የተቀናጀ እርምጃ ለመውሰድ በ’Quad’ በኩል እየሰራን ነው” ሲሉም አክለዋል።