መካከለኛ ምስራቅ
በእስራኤልና ሐማስ የተኩስ አቁም ስምምነት ቢፈፀምም የእስራኤል ሰራዊት በጋዛ ድብደባ እንዳላቋረጠ ተገለፀ።
እስራኤል በሊባኖስ ላይ ጥቃት እንደፈፀመች እየተገለፀ ይገኛል።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 07/02/2018፡- የእስራኤል ሰራዊት አሁንም በአንዳንድ አከባቢዎች ድብደባ እያካሄደ እንደሚገኝና ከስደት የተመለሱ ፍልስጤማዊያን በከባድ ስጋት ውስጥ እንደሚገኙ ለአልጄዚራ ተናግሯል።
እንዲሁም እስራኤል በሊባኖስ ላይ ጥቃት መሰንዘሯ መረጃዎች አሳይቷል።
በደቡባዊ እና ምስራቃዊ ሊባኖስ የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች አካባቢውን ሲያጠቁ ቢያንስ አንድ ሰው ሲገድል ከፍተኛ ፍንዳታዎች ታይተዋል።
ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰ ግን የተገለፀ ነገር ነለም።
ጥቃቲን ተከትሎ ኢራን መግለጫ ሰጥቴለች።
የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እስማኢል ባቃኢ እንዳሉት እስራኤላውያን በደቡባዊ ሊባኖስ ላይ ያደረሱት ጥቃት “የሊባኖስን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ላይ ግልጽ ጥሰት ነው” ብለዋል።