ኢኮኖሚ

የሱዳኑ ታርኮ አየር መንገድ እ.አ.አ. ከጥቅምት 20 ጀምሮ ከፖርት ሱዳን ወደ አዲስ አበባ ቀጥታ በረራ እንደሚጀምር አስታወቀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 04/02/2018፡- ታርኮ አየር መንገድ ከሰኞ ጥቅምት 20 ቀን 2025 ጀምሮ በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ እና በጊዜያዊቷ የአስተዳደር ዋና ከተማ ፖርት ሱዳን መካከል ቀጥተኛ በረራ እንደሚጀምር አስታውቋል።

ይህ እርምጃ በሱዳን እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የጉዞ እና የንግድ ልውውጥ ለማሳደግ ያለመ ነው ብለዋል።

በአዲስ አበባ የታርኮ አየር መንገድ ቀጠኛዊ ስራ አስኪያጅ ኦማር አህመድ ኢድሪስ፥ የአዲሱ መስመር መጀመር የኩባንያው ቀጣናዊ ትስስር ለማስፋት እና ሱዳንን ከበርካታ የአፍሪካ መዲናዎችና ከተሞች ጋር ለማገናኘት ያለመ እቅድ አካል መሆኑን አብራርተዋል።

ይህ መስመር የሁለቱን ሀገራት ኢኮኖሚያዊና የንግድ ግንኙነት ለማጠናከር እና የነጋዴዎችን እና የመንገደኞችን እንቅስቃሴ ለማቀላጠፍ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንደሚያበረክትም ጠቁመዋል።

ኢድሪስ አክለውም ታርኮ አየር መንገድ በአዲስ አበባ እና በፖርት ሱዳን መካከል ከሚያደርገው አዲስ በረራ በተጨማሪ ወደ አስመራ መደበኛ በረራ በማድረግ ቀጣናዊ ትስስርን በማሳደግ ተጓዦችን ሱዳንን ከጎረቤት ሀገራት ጋር ለማገናኘት ሰፊ አማራጮችን በመስጠት ላይ ይገኛል ብለዋል።

የአየር ደህንነት እና የተሳፋሪ ምቾትን በጠበቀ መልኩ ለደንበኞቹ ከፍተኛ ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት ጥረት እንደሚያደርግ አጽንኦት ሰጥቷል።

ታርኮ አቪዬሽን ታዋቂ ከሆኑ የሱዳን አየር ማጓጓዣዎች አንዱ ሲሆን፣ ወደ በርካታ የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት መደበኛ በረራዎችን የሚያደርግ፣ እና በቀጣይነት አገልግሎቱን ለማስፋት እና ቀጠናዊ ትስስሩን ለማጠናከር እየተጋ መሆኑን አስታውቀዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates