አፍሪካ

አል ሲሲ በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ትራምፕ ለተጫወቱት ሚና የግብፅን ከፍተኛ የክብር ሽልማት ሊሰጧቸው ነው ተባለ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 04/02/2018፡- የግብፁ ፕሬዝደንት አብዱል ፋታህ አል ሲሲ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጋዛ ሰላምን በማስፈንና ጦርነቱን በማስቆም ረገድ ላሳዩት ሚና እውቅና ለመስጠት በሀገሪቱ ከፍተኛ የሆነውን ‘ናይል ኮላር’ የተሰኘ የክብር ሽልማት ለመስጠት መወሰናቸውን የግብፅ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

አል ሲሲ ለትራምፕ የሀገሪቱን ከፍተኛ ሽልማት ለመስጠት ማሰባቸው ይፋ የተደረገው ግብፅ በፕሬዝደንት ኤል ሲሲ እና በአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በጋራ የሚመራውን የመጪውን የሰላም ጉባኤ ለማካሄድ ከ20 በላይ የሚሆኑ የሀገራት መሪዎችን ለመቀበል በምትዘጋጅበት ወቅት ነው።

‘ናይል ኮላር’ የግብፅ ከፍተኛ እና እጅግ የተከበረ መንግሥታዊ ሽልማት ሲሆን፣ ለግብፅ ወይም ለዓለም የላቀ አገልግሎት ለሰጡ ግለሰቦች በፕሬዝደንታዊ አዋጅ የሚሰጥ ነው። ቀደም ሲል ይህን ሽልማት ከተቀበሉ ዓለም አቀፍ ግለሰቦች መካከል የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ  አጼ ኃይለ ሥላሴ፣ የዮርዳኖሱ ንጉሥ ሁሴን፣ ግርማዊት ዳግማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ እና የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር ይገኙበታል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates