ኢኮኖሚ

ባለሙያዎች በአፍሪካ አፋጣኝ የእዳ ስረዛ እንዲደረግ ጠየቁ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 04/02/2018፡- ከ30 በላይ መሪ ኢኮኖሚስቶች እና ባለሥልጣናት፣ የአፍሪካ ሀገራት በአማካይ 17% ዓመታዊ ገቢያቸውን ዕዳ ለመክፈል ማዋላቸውን በመቃወም፣ አፋጣኝ የእዳ ስረዛ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

የኖቤል ተሸላሚው ጆሴፍ ስቲግሊዝን ጨምሮ ባለሙያዎቹ፣ ይህ ከፍተኛ የዕዳ ጫና መንግስታት ለመሰረታዊ አገልግሎቶች የሚሰጡትን ድጋፍ እየገታ እንደሆነ አስጠንቅቀዋል።

ይህም ሆኖ 32 የአፍሪካ ሀገራት ከጤና፣ እና 25 ሀገራት ከትምህርት ይልቅ ለዕዳ እንዲከፍሉ እየገፋፋ መሆኑም ጠቁመዋል።

ባለሙያዎቹ፣ የዕዳ ቅነሳ ከተደረገ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች ንፁህ ውሃ ማቅረብ እና በሺዎች የሚቆጠሩ የሕፃናትን ሞት መከላከል እንደሚቻል አስታውቀዋል።

ጥሪው የቀረበው በአፍሪካ የጤና ሥርዓት የመድኃኒት እጥረት እና የሰራተኞች ችግር በገጠመበት ወቅት ነው።

በሚቀጥለው ወር በአለም ባንክ እና በአይኤምኤፍ አመታዊ ስብሰባዎች ላይ ሀገራት ይህንን ጉዳይ እንዲፈቱት ጥያቄው ቀርቧል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates