አፍሪካ

የሱዳኑ ፈጥኖ ደራሽ ሐይል ከኤል ፋሸር የሚሸሹ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎችን በስለላ ክስ ማሰሩን ምንጮች ገለጹ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 04/02/2018፡- የሱዳን የፈጣን ድጋፍ ሃይሎች በሰሜን ዳርፉር ኤል ፋሸር ከተማ ሲሸሹ የነበሩት በደርዘን የሚቆጠሩ ሲቪሎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአካባቢው ምንጮች እና ቤተሰቦቻቸው መግለፃቸው ተዘግበዋል።

የአካባቢው ምንጮች እና የታሳሪዎቹ ዘመዶች ለሱዳን ትሪቡን እንደተናገሩት ታጣቂ ሐይሉ ከኤል ፋሸር በስተደቡብ በምትገኘው ዳር ኢሳላም ከተማ ወደ 70 የሚጠጉ ንፁሀን ዜጎችን በቁጥጥር ስር አውሏል። አብዛኞቹ ከቅያቸው የተፈናቀሉት ሲሆኑ ከሱዳን ሠራዊት ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል እንዳሰራቸው ታውቀዋል፡፡

“ፈጣን ደራሽ ሐይሉ እሁድ እና ሰኞ መጠነ ሰፊ የእስር ዘመቻ አድርጓል… ይህም በደርዘን የሚቆጠሩ ሲቪሎች ላይ ኢላማ ያደረገ ሲሆን አብዛኞቹ ከኤል ፋሸር የሚሸሹ ወጣቶች ነበሩ” ሲል አንድ የዓይን እማኝ ተናግሯል። የተወሰኑት ወደ ደቡብ ዳርፉር ዋና ከተማ ኒያላ እንደተዛወሩም አክለዋል።

አንዳንድ ቤተሰቦች ዘመዶቻቸው እንዲፈቱ 15 ሚሊዮን የሱዳን ፓውንድ ቤዛ እንዲከፍሉ ከታጣቂ ሐይሉ ጥሪ እንደደረሳቸው ሀገባው አመልክተዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates