ኢትዮጵያ
የኒውኩሌር ሐይል ኮሚሽን ማቋቋሚያ ደንብ ፀደቀ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 04/02/2018፡- የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 4 ቀን 2018 ባካሄደው መደበኛ ስብስባ ሦሥት ከእነዚህ አንዱ የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽንን የሚያቋቁም ደንብ ነው።
ምክር ቤቱ በደንቡ ከተወያየ በኃላ በነጋሪት ጋዜጣ ከታተመበት ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን አፅድቀዋል፡፡
ደንቡ የጸደቀው ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የኒውክሊየር ኃይል ማመንጫ “ለማቀድ እና ለመገንባት” የሚያስችል ሰነድ በተፈራረሙ በኃላ ነው ተብለዋል።
ዛሬ በጸደቀው ደንብ መሰረት የሚቋቋመው ኮሚሽን፤ ኢትዮጵያ የኒውክሊየር ቴክኖሎጂን ከዓለም አቀፍ ማዕቀፎች በተጣጣመ መልኩ “ለሰላማዊ መንገድ” ለመጠቀም የምታደርገውን ጥረት “የመምራት እና የማስተባበር ኃላፊነት” እንደተጣለበት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
ኢትዮጵያ የኒውክሊየር ኃይልን ለኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት፣ ለኢንዱስትሪ ልማት፣ ለምግብ ዋስትና፣ ለጤና አገልግሎት፣ ለሳይንስ እና ምርምር ዘርፎች ለመጠቀም እንዳቀደች ጽህፈት ቤቱ ዛሬው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል
በዚህ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ አቶ ሳንዶካን ደበበ የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር አድርገው ሾመዋል።