መካከለኛ ምስራቅ

” በጋዛ ጦርነቱ አክትሟል ”  አሉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ።

ትራምፕ በእስራኤል ፓርላማ ደምቋል።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 03/02/2018፡- በሐማስ ታግቶ በህይወት የነበሩት 20 እስራኤላዊያን ተለቋል።

ከ2 ዓመት በፊት መስከረም 26 ቀን 2016 ዓ.ም. ሐማስ በምዕራብ እስራኤል ድንገተኛ ጥቃት ፈጽሞ 1,200 ሰዎችን ከገደለ እና 251 አግቶ ከወሰደ በኋላ እስራኤል በጋዛ መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ ስታካሂድ መቆየቷ ይታወሳል።

በዚህ ወታደራዊ ዘመቻም 67,000 ፍልስጤማውያን ሲገደሉ ከእነዚህ መካከልም 18,000 ያህሉ ሕጻናት መሆናቸውን በሐማስ የሚመራው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

አስከፊው ጦርነት እንዲቆም ብዙ ጥረት ቢደረግም ፍሬ ሳያፈራ ቆይቷል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን ከመጡ በኃላ ከሌሎች ሀገራት ጋር ሆነው ብዙ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተው እስራኤል እና ሐማስ ከቀናት በፊት የተኩስ አቁም ስምምነት አድርገዋል።

በመጀመሪያው ስምምነት መሰረት ሀማስ ያገታቸውን እስራኤላውያን ይለቃል እስራኤልም አጉራ ያሰረቻቸውን ፍልስጤማውያንን ትለቃለች ተብሏል።

ዛሬ 20 እስራኤላውያን ታጋቾች በሀማስ ተለቀው ለቀይ መስቀል ተሰጥተዋል።

በስምምነቱ ትልቅ ሚና የነበራቸው ዶናልድ ትራምፕም እስራኤል ገብተዋል።

ቴላቪቭ ሲደርሱ የእስራኤል ጠ/ሚ ቤኒያሚን ኔታንያሁ ተቀብለዋቸዋል።

ትራምፕ እስራኤል ለመሄድ ወደ ኤርፎርስ ዋን አውሮፕላን እየተሳፈሩ እያለ የተኩስ አቁሙ እንደሚፀና እና በጋዛ በፍጥነት ” የሰላም ቦርድ ” እንደሚቋቋም ተናግረዋል።

” በጋዛ ጦርነቱ አክትሟል ” ሲሉም ተደምጠዋል።

ጋዛን ሙሉ በሙሉ እንድትወድም ትልቅ አስተዋፀኦ ያደሰጉት ትራምፕ በሚቀጥሉት አስርት ዓመታት ውስጥ ጋዛ ” ተአምር ” ትሆናለች ብለው እንደሚያስቡ ተናግረዋል።

ወደተለያዩ አከባቢዎች ተሰዶ የነበሩት ፍልስጤማዊያን ወደ ጋዛ እየተመለሱ ሲሆኑ ጋዛ ግን እንደተዉዋት አላገኟትም።

ህንፃዎቿ ፈራርሶ ወደ ምድረ ባዳ ተቀይራለች።

እስራኤላዊያን ተኩስ ቁሞ ወደ ቀያቸው መመለሳቸው ቢያስደስታቸውም ለአመታት የገነቧት ጋዛ አሁን ሲመለኳት ደግሞ ልባቸው ዳግም ደምቷል።

ቢሆንም በጋዛ ውስጥ ከአሁኑ የመንገዶች ግንባታ ተጀምሯል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates