ዲፕሎማሲ
ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ኅብረት ስትራቴጂካዊ የትብብር ስምምነት መፈራረማቸው ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 29/01/2018፡- ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ማጠናከር የሚያስችላቸውን “ግሎባል ጌትዌይ ፓርትነርሺፕ” የትብብር ስምምነት መፈራረማቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቋል።
ስምምነቱን ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ እና የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌይን ፈርሞታል።
ይህ ስምምነት በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ህብረት መካከል ላለው የረጅም ጊዜ አጋርነት አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት እንደሆነም ተጠቁሟል።
ስምምነቱ በዲጂታላይዜሽን፣ በታዳሽ ኃይል፣ በምግብ ሥርዓት፣ በጤና በመሰረተ ልማት እንዲሁም በሰላምና ጸጥታ ሁለቱ ወገኖች ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ከስትራቴጂያዊ አጋርነት ስምምነቱ አስቀድሞ ፕሬዚዳንት ታዬ እና ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸው ተሰምቷል፡፡