መካከለኛ ምስራቅ

እስራኤልና ሀማስ ተኩስ ለማቆም መስማማታቸው ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 29/01/2018፡- እስራኤልና ሀማስ ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረውንና በጋዛ ጦርነት እንዲያበቃ በፕሪዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቀረበውን የመጀሪያውን ዙር የተኩስ አቁም ስምምነት መስማማታቸው ተገለጸ።

በዚህም የሀማስ እስረኞችንና የእስራኤል ታጋቾችን ለመለዋወጥ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

ስለሆነም ሀማስ በሕይወት ያሉ 40 እስራኤላውያን ታጋቾችን በ72 ሰዓታት ውስጥ እስከቀጣይ ቅዳሜ ለመልቀቅ የተስማማ ሲሆን እስራኤል በበኩሏ ጦሯን ከጋዛ ለማስወጣት መስማማቷን ሮይተርስ ዘግቧል።

67 ሺሕ ሰው ያለቀበትን የጋዛ ደም አፋሳሽ ጦርነት ያስቆማል በሚል ተስፋ የተጣለበት ስምምነት በፍልስጤማውያንና እስራኤላውያን ዘንድ ከፍተኛ ደስታን ፈጥሯል።

በርካታ ፍልስጤማውያንና የጋዛ ነዋሪዎች በአደባባይ ወጥተው ደስታቸውን ሲገልጹ ታይተዋል።

ትናንትና በግብጽ በተካሄደው የእስራኤልና ሀማስ የተኩስ አቁምና እስረኞችንና ታጋቾችን የመለዋወጥ ስምምነት ፊርማ ፕሬዚዳንት ትራምፕ “ከፍተኛ ኩራት ይሰማኛል” ሲሉ ገልፆታል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates