የተለያዩ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 25 በመቶ የሚሆነውን የአለም ሰላም አስከባሪ ሃይሉን ሊቀንስ ነው።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 29/01/2018፡- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም አስከባሪ ኃይሉን እና ኦፕሬሽኖችን ማጠፍ ይጀምራል ተብሏል።

በሚቀጥሉት ወራቶች ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች ርቀው የሚገኙበትን ዓለም አቀፍ የትኩረት ቦታዎች ለቀው እንዲወጡ ይገደዳሉ ተብሏል።

ምክንያቱ ደግሞ አሜሪካ የምትሰጠው የነበረውን ድጋፍ በከፍተኛ ደረጃ በመቀነሱ ነው።

በዚህ የገንዘብ ድጋፍ እጥረት ምክንያትም በሚቀጥሉት ወራት በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ለቀው እንዲወጡ ያስገድዳል ሲሉ አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን ተናግረዋል።

በዘጠኝ የሰላም ማስከበር ቦታዎች ከተሰማሩት ከ50,000 በላይ የሰላም አስከባሪ ሃይሎች ከ13,000 እስከ 14,000 የሚደርሱ ወታደራዊ እና የፖሊስ አባላት ወደአገራቸው እንደሚመለሱ መረጃው አሳይቷል።

በሶማሊያ የሚገኘው የተመድ ድጋፍ ሰጪ ቢሮም የዚህ ውሳኔ ሰለባ እንደሚሆን ታውቋል።

የተባበሩት መንግስታት የዚህ ዓመት የሰላም አስከባሪ ሃይል በጀቱን በ15 በመቶ ለመቀነስ ማቀዱን ተገልጿል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates