ኢኮኖሚ
የኢቲሃድ አየር መንገድ ከአቡ ዳቢ ወደ አዲስ አበባ ዕለታዊ በረራ መጀመሩ ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 29/01/2018፡- የኢቲሃድ አየር መንገድ ወደ አዲስ አደባ በረራ የጀመረው ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ስምምነት ማድረጉን ተከትሎ ነው።
ስምምነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ወደ አቡ ዳቢ ዛይድ አለም አቀፍ አየር ማረሪያ እንዲሁም ኢትሃድ አየር መንገድ ከአቡዳቢ-አዲስ አበባ ቀጥታ የበራራ አገልግሎት መጀመር የሚያስችል ነበር።
በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ዛይድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሚያደርገውን በረራ ባለፈው ሐምሌ የጀመረ ሲሆን የኢቲሃድ አየር መንገድ ደግሞ ትናንት መስከረም 28 ቀን 2018 ዓ/ም ወደ አዲስ አበባ የሚያደርገውን ዕለታዊ በረራ መጀመሩን ታውቋል።
በበረራ ማስጀመሪያ ሥነሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንዲሁም የኢቲሃድ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አንቶናልዶ ኔቬስ ተገኝተዋል።