ኢትዮጵያ

በአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ ከ17 በመቶ የማይበልጥ መሆኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ።

በነገው ዕለት ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነትን በይፋ የምትጀምር መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታወቋል።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 28/01/2018፡- በአፍሪካ አህጉር የሚደረገው የእርስ በርስ የንግድ ለውውጥ ገና ያልተሰራበትና ከ17 በመቶ ያልበለጠ መሆኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገልጿል።

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ያስሚን ወሀብረቢ አሁን የተደረሰው የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነት በሀገራቱ መካከል የሚደረገውን የንግድ እንቅስቃሴ ከፍ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሌላው የአህጉሩ ሀገራት ከሌሎች ጋር የሚደርጓቸው የንግድ እንቅስቀሴዎች 67 በመቶ ሲደርስ በአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለው የእርስ በርስ ንግድ ግን ከ17 በመቶ የማይበልጥ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የምታደርገው ንግድ ዝቅተኛ ሆኖ በአንፃሩ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላት ልውውጥ የተሻለ የሚባል መሆኑን ጠቅሰዋል። ይህም ስምምነት የሀገራቱን የንግድ እንቅስቃሴ የሚጨምር መሆኑን ጠቁመዋል።

በስምምነቱ ውስጥ ከ55 በላይ ሀገራት መኖራቸውን ገልጸው፤ ከ1 ነጥብ 4 ቢልየን በላይ ሕዝብ ያቀፉ፤ ከ3 ነጥብ 4 ትሪልየን ዶላር ጥቅል የሀገር ውስጥ ምርት የሚበልጥ ትልቅ የኢኮኖሚ አቅም ያለው መሆኑን አንስተዋል።

ይህ ስምምነት ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈረመው በሩዋንዳ ኪጋሊ በአውሮፓውያኑ 2018 መሆኑና ኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ፈራሚ መሆኗን ሚኒስትር ዴኤታዋ ያስሚን ገልጸዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates