Uncategorized

የፈረንሳዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰባስትያን ሌኮርኑ አንድ ወር ሳይሞላቸው ሥልጣን መልቀቃቸው ተሰማ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 27/01/2018፡- ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካቢኔያቸው ይፋ በተደረገ በአንድ ቀን ውስጥ ሥልጣን መልቀቃቸውን አስታውቀዋል።

“ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኜ ለመቀጠል የሚያስችል ሁኔታ አልተሟላም” ሲሉ ለሥልጣናቸው መልቀቅ ምክንያት የሆናቸውን ገልጸዋል።

ሌኮርኑ ከፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ለአንድ ሰዓት የዘለቀ ውይይት ካደረጉ በኋላ ከሥልጣን መልቀቃቸው በይፋ ተገልጿል::

ጠቅላይ ሚንስትሩ ያዋቀሩት አዲሱ መንግስት ሚንስትሮች ስራ ከመጀመራቸው አስቀድሞ በዚህ ሳምንት ከፓርላማ የመተማመኛ ድምጽ ማጣቱ ተነግሯል።

Show More

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates