
ኢትዮ ሞኒተር፡ 21/01/2018፡- የጠቅላይ ሚኒስትር የምስራቅ አፍሪካ አማካሪው አቶ ጌታቸው ረዳ ለሕክምና በዱባይ ሆኖ Global Power Shift ለተሰኘው የዜና ማእከል የሰጡት ቃለ ምልልስ ብዙዎች እያነጋገረ ነው።
አቶ ጌታቸው ካነሱዋቸው ጉዳያች አንዱ የህወሐትና ሻዕቢያ አመራሮች ግንኙነት የተመለከተ ሲሆን “የህወሐት አመራሮች ከፌደራል መንግስት ይመጣል ብለው ከሚያስቡት እውነተኛ ወይም ምናባዊ ስጋት እራሳቸውን ለማዳን፣ ከኤርትራውያን ጋር ህብረት መፍጠር ይቻል እንደሆነ ማየት ነው” ብሏል።
“ኤርትራውያን በጣም ብልሆች ናቸው። የፌደራል መንግስትን በቀጥታ የመዋጋት የሰው ኃይል ብልጫ እንደሌላቸው ያውቃሉ። ስለዚህ፣ ሀገሪቱን ለማናጋት በድንበራቸው ማዶ ያሉ የፖለቲካ መጠቀሚያዎችን (useful idiots) መጠቀም ይፈልጋሉ” ሲሉም ተደምጧል አቶ ጌታቸው ረዳ።
“የጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት በነበርኩበት ወቅት፣ ከኤርትራውያን ጋር ግንኙነት ጀምሬ ነበር ያሉት ሚኒስትሩ ተስፋዬም፣ ሌላ ዙር ጦርነት በትግራይ ላይ እንዳይከሰት መከላከል ነበር፤ ምክንያቱም ለትግራይ ሕዝብ የማይሽር ጠባሳ እንደሚተው ነበር የማየው” ብሏል።
“የህወሓት አመራሮች በትግራይ ህዝብ ዋጋ ሻዕቢያን ለማዳን የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ለማቆም መስዋእትነት መክፈል ካለብኝ እከፍላለሁ” ሲሉም ተደምጧል።