አፍሪካ

ኤርትራ በባህር ተደራሽነት ሰበብ የሚደረግ የማስፋፋት አባዜ መቆም አለበት አለች።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 20/01/2018፡- የኤርትራው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በጋራ ጥቅምና ስጋቶች ላይ መወያየታቸው ተገልጿል።

ሚኒስትሩ ዑስማን ሳልህ “የባህር መዳረሻ” በሚል ስም ግዴለሽ ቅስቀሳዎች እና የመስፋፋት ምኞቶችን እየተሰሙ መሆናቸው በመጥቀስ ኤርትራ በማንኛውም ሁኔታ ወደ እንደዚህ ዓይነት ግድየለሽነት አጀንዳዎች አትጋበዝም በማለት በድጋሚ የአገራቸው አቋም መግለፃቸው ተሰምቷል።

ዋና ፀሐፊው አንቶኒዮ ጉተሬዝ በበኩላቸው፣ ኤርትራ በቀጣናው ሰላምና ደኅንነት ላይ የምታደርገውን አዎንታዊ ተሳትፎ አድንቆ፣ የተባበሩት መንግስታት በሁሉም አገሮች የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነትን መርሆች ፅኑ መሆኑ መግለፃቸው የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገ/መስቀል አስታውቋል።

ሁለቱም ወገኖች በኤርትራ እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት መካከል ያለውን ጠንካራ አጋርነት እና ትብብር አድንቀው ይህንን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት መግለፃቸው ተሰምቷል።

የኤርትራው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት/ኦቻ ረዳት ዋና ፀሀፊ ወይዘሮ ጆይስ ሙሱያንም አነጋግረዋል።

ውይይቱ በመንግስት እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ ትብብር ላይ እንደሆነ የገለፀው ዘገባው ኦቻ የበጀት እጥረቶች ቢኖሩትም ከኤርትራ ጋር ነአየር ንብረት ለውጥ የመቋቋም ፕሮግራሞች ላይ በቅርበት ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጧል፧።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates