ጤና

ኢትዮጵያ እና ጣሊያን የ4.1 ሚሊዮን ዩሮ ስምምነት መፈራረማቸው ተሰማ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 20/01/2018፡- ኢትዮጵያ እና ጣሊያን የሽሬ እና የጎንደር ሆስፒታሎችን የጤና አጠባበቅ አገልግሎት ለማጠናከር የሚውል የ4.1 ሚሊዮን ዩሮ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን ትናንት መስከረም 19 ቀን 2018 ዓ.ም የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሺዴ እና በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓሌሴ ፈርመዋል።

በዚሁ ወቅት ንግግር ያደረጉት አቶ አሕመድ ሺዴ፤ ስምምነቱ በተለይም በትግራይ እና በአማራ ክልሎች በግጭት ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚሰጠውን የጤና አገልግሎት ለማሻሻል እንደሚጠቅም ገልፀዋል።

በስምምነቱ መሰረት የሚከናወኑ ሥራዎችም ከ15 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የሚቀርበውን የጤና አጠባበቅ አገልግሎት ለማሻሻል እንደሚያግዙ ተናግረዋል።

በተለይም እናቶች በተሻለ አገልግሎት እንዲወልዱ፣ ሕጻናት ሕይወት አድን እንክብካቤ እንዲያገኙ እና ተፈናቃዮች አስፈላጊውን የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል ሲሉ መግለጻቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates