ዲፕሎማሲ

ማሌዥያ በአዲስ አበባ የሚገኘውን ኤምባሲዋን ከ43 ዓመታት በኋላ መክፈቷ ተገለፀ።

ማሌዥያ በአዲስ አበባ የነበራትን ኤምባሲ ከ43 ዓመታት በኋላ ዳግም በይፋ ከፈተች።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 19/01/2018፡- የማሌዥያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ መስከረም 19 ቀን 2018 ባወጣው መግለጫ፣ ኤምባሲው ከ መስከረም 13  ቀን 2018 ጀምሮ ሥራ መጀመሩን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣን ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለጹት፣ ማሌዥያ በአውሮፓውያኑ 1982 ዓ.ም. ከነበረው የደርግ ሥርዓት ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷ በመሻከሩ ምክንያት ኤምባሲዋን ዘግታ ነበር።

የማሌዥያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው፣ “የኤምባሲው ዳግም መከፈት ማሌዥያ ከኢትዮጵያ ጋር  የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው። እንዲሁም፣ በንግድ፣ በኢንቨስትመንትና በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ላይ፣ የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያስገኙ የትብብር ዘርፎች አዳዲስ ዕድሎችን ለማሰስ  ይረዳል” ብሏል።

መግለጫው አክሎም፣ የአፍሪካ ኅብረት ዋና መሥሪያ ቤት መቀመጫ በሆነችው አዲስ አበባ የኤምባሲው ዳግም መከፈት፣ ከአኅጉራዊው ተቋም ጋር ለመሥራት አዳዲስ መንገዶችን ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል ሲል ገልጿል። ኤምባሲው ለጊዜው ሥራውን እያከናወነ ያለው በሸራተን አዲስ ሆቴል ውስጥ በሚገኝ ጊዜያዊ ጽህፈት ቤት ውስጥ ነው ተብሏል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates