የተለያዩ
በትግራይ በተፈናቃዮች ካምፕ ዛሬ ያጋጠመውን አሳዛኝ ፍፃመ ብዙዎች እያነጋገረ ይገኛል።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 13/01/2018፡- ዛሬ መስከረም 13 ቀን 2018 ዓ/ም ከጡዋቱ 12:30 አንድ አውሬ በኬንዳ ውስጥ ወደተኙ ሁለት ህፃናት ዘሎ ይገባል።
ህፃናቱ የአራትና ሁለት ዓመት ታላቅና ታናሽ ናቸው። ህፃናቱ በተኙበት ግን ጅብ ገብቶ ታላቁን ትቶ መሸከም የሚችለውን ታናሹን ለይቶ ይዞት ይሮጣል።
የአራት ዓመቱ ታላቅ በድንጋጤ ራቁቱን ወደ ውጭ ወጥቶ ሲጮህ ጎረቤቶች ጅቡን ተከትሎ ቢረጡም የህፃኑን ህይወት ግን ሊያድኑት አልቻሉም።
ይህ 70 ካሬ እየተባለ በሚጠራው የምዕራብ ትግራይ ተፈናቃዮች ካምፕ ያጋጠመው አሳዛኝ ክስተት ተፈናቃዮችን ተጨማሪ ስጋት ፈጥሯል።
ጅቦቹ በተደጋጋሚ ኬንዳ ቤቱን ገብተው ዶሮዎችን ይወስዱ እንደነበሩ የሚገልፁት ተፈናቃዮቹ አሁን ደግሞ የናኦድ ሃ/ስላሴ ህይወትን ነጥቋል ብሏል።
የህፃን ናኦድ ወላጆች ከምዕራብ ትግራይ ዞን ተፈናቅለው በመጠለያው ውስጥ ከአምስት ዓመታት በላይ ቆይተዋል።
የችግሩ መንስኤም ቦታው ያልተጠበቀና አስተማማኝ ባለመሆኑ ነው ይላሉ።
ችግሩ በፍጥነት ካልተቀረፈም ሌሎች የተፈናቀሉ ህጻናትም ተመሳሳይ እጣ ሊገጥማቸው ይችላል ሲሉ ስጋታየው ገልጿል።
ተፈናቃዮቹን ለመታደግ የሚመለከታቸው አካላት መፍትሄ እንዲፈልጉም ተማፅኗል።
የሕፃን ናኦድ ወላጆች ለ 5 ዓመታት በኬንዳ ሲኖሩ የልቅሶአቸውን ድንኳንም በኬንዳው ውስጥ ሆኗል።