ኢትዮጵያ

ኤርትራ ለኢትዮጵያ ምላሽ ሰጠች፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 13/01/2018፡- የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስትር የማነ ገብረመስቀል፣ የኢትዮጵያው ገዥ ፓርቲ ብልጽግና ባለስልጣናት ባሕር በር ለማግኘት በሚል “ቀጠናዊ ቀውስ ለመፈብረክ የሚያደርጉት ጥረት ባኹኑ ወቅት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል” በማለት በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ከሰዋል።

የብልጽግና ባለሥልጣናት በባሕር በር ዙሪያ በየዕለቱ “አሳሳች” እና “ተንኳሽ” ንግግሮችን ያደርጋሉ ያሉት የማነ፣ ከባለስልጣናቱ ንግግሮች መካከል አንዱ “የኤርትራን ታሪክ መከለስ” እና “አዛብቶ ማቅረብ” ይገኝበታል ብለዋል።

“የቅኝ ግዛት ድንበሮች ጨምሮ የዓለማቀፍ ሕግጋትን ዋና ዋና መርሆዎችን ሆነ ብሎ መጣስ” እና “ግዴለሽ የጦርነት ዛቻ” ሌላኛዎቹ የብልጽግና ባለስልጣናት ትርክቶች መለያ ባሕሪያት እንደሆኑ የማነ ገልጸዋል።

የማነ አያይዘውም፣ የአፍሪካ ቀንድ ቀጠና፣ “አላስፈላጊ” እና “ማስቀረት የሚቻል” ሌላ ዙር ግጭትና ትርምስ ውስጥ ሊገባ አይገባውም በማለት አሳስበዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates