አውሮፓ
የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን ከእስራኤል ነፃ የንግድ ልውውጥ ለማቆም መወሰኑ ተሰማ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 09/01/2018፡- የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ከእስራኤል ጋር ነፃ የንግድ ልውውጥን ለማቆም እና በሁለት የእስራኤል ሚኒስትሮችን ማዕቀብ እንዲጥል ሀሳብ ማቅረቡ ተሰማ።
ይህም በእስራኤል እና በአውሮፓ ህብረት ግንኙነት ላይ ትልቅ ጉዳት የሚያስከትል እርምጃ ነው ተብሏል።
የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን ሃሳቡን ለአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ካቀረቡ በኋላ “በየቀኑ በጋዛ ውስጥ የሚፈጸሙት አሰቃቂ ድርጊቶች መቆም አለባቸው” ብለዋል።
“አፋጣኝ የተኩስ አቁም፣ ለሁሉም ሰብዓዊ እርዳታዎች ያልተገደበ ተደራሽነት እና በሃማስ የተያዙ ታጋቾችን በሙሉ መልቀቅ ያስፈልጋል” ሲሉም ተናግሯል።
እርምጃው የተወሰደው የእስራኤል ወታደሮች በጋዛ ከተማ ላይ የመሬት ጥቃት ከከፈቱ ከአንድ ቀን በኋላ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባደረገው ትልቅ ምርመራ እስራኤል በዘር ማጥፋት ወንጀል ጥፋተኛ መሆኗን ካረጋገጠ በኋላ ነው።