ኢትዮጵያ
የኢንግሊዝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ጉዳይ “ከተሳሳተ ስሌት” ትታቀብ ሲሉ ማስጠንቀቃቸው ተሰማ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 09/01/2018፡- የኢንግሊዝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተደርገው የተሾሙት የቀድሞው የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስተር የነበሩት ዴቪድ ላሚ የኢትዮጵያ አቻቸው የነበሩትን ዶ/ር ጌዲኦን ጥሞቴዎስን ማስጠንቀቃቸው ተነገረ።
ላሚ የተሳሳተ ስሌት ያሉትን የኢትዮጵያ የቀይ ባህር መሻት በማጣጣል ከኤርትራ ጋር ገንቢ ውይይት እንዲደረግ ጌዲዮን ጥሞቴዎስን ቀጥታ ማስጠንቀቃቸው ተሰምቷል።
በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል አዲስ ስለተፈጠረው ውጥረት አስመልክቶ የዩኬ ፓርላማ ከትናንት በስቲያ በተወያየበት ወቅት ያለፈው ነሐሴ ወር ተመሳሳይ ምክር ለኤርትራም እንዲደርስ ተደርጓል ብሏል።
አዲስ ኢስታርድ እንዳስነበበው የዩኬ መንግስት ተጠሪ የሆኑት ጄራርድ አንቶኒ ሌሞስ በፓርላማው በጉዳዩ ላይ የመንግሥታቸው አቋም በተመለከተ ለተነሳላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ፦
“የመንግስት አቋም ሀገራት በድርድር እና በሰላማዊ መንገድ ለንግድ የሚሆን የባህር አክሰስ ማግኘት አለባቸው የሚል ነው። እንግሊዝ የሀገርን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት አደጋ ላይ የሚጥሉ አመፅ ድርጊቶችን ወይም ንግግሮችን አትደግፍም” ሲሉ መልሰዋል።