ኢትዮጵያ

የአባይ ውሃ ‘ጦርነት’ አብቅቷል። በዚህም ኢትዮጵያ አሸነፈች ሲል the arab weeks.com የተሰኘ ድህረ ገፅ አስነበበ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 08/01/2018፡- “የግብፅ እጆች ከታሰሩ የሱዳን ተሰብረዋል” የሚለው ዘገባው ከአስር አመታት በላይ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በዘመናዊ ታሪክ ውስጥ ትልቁ የውሃ ጦርነት ነው ብለው ብዙዎች ያምኑበት ለነበረው የህዳሴ ግድብ ሒሳብ ተከፍሏል ይላል።

ትረካው አሳማኝ እና ቀላል ነበር፡ ወደ ላይ እየወጣ ያለው ሃይል ኢትዮጵያ ታሪካዊውን የታችኛውን ተፋሰስ አገራት የበላይነት የሚቀይር ትልቅ ግድብ እየገነባች ነበር፣ ይህም ወደ ግጭት እንዳያመራ ስጋት እንደነበር ይገልፃል።

ሆኖም ያ ታሪክ አሁን በይፋ ታሪክ ሆኖ አልፏል የሚለው ዘገባው ፣  የግብፃውያን የቆዩ ተፅዕኖ ፈጣሪ እጆች አሁን ተሰባብረዋል ይላል።

የታችኛው ተፋሰስ ኅብረት ፈርሷል፣ ዓለም አቀፍ ሽምግልና ተንኖአል፣ አዲስ፣ ውስብስብ የሆነ ጨዋታ አሁን በአባይ ሸለቆ ላይ እየተካሄደ ነው እንደሚገኝም አውስቷል።

በዚህ አዲስ እውነታ ውስጥ በጣም አስፈላጊው ነገር ለግብፅ ወታደራዊ ምርጫ በትክክል መዘጋቱ እንደሚያሳይ የገለፀው መረጃው በአንድ ወቅት አርዕስተ ዜናዎችን ሲቆጣጠር የነበረው ያለፈው የቤሊኮዝ ንግግር አሁን መና ቀርቷል ብሏል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ግብፅ ይህን ግድብ ትደረምሰዋለች” ብለው የተናገሩትን ንግግር በካይሮ እየተገመገመ የነበረውን የፖሊሲ አማራጭን ያንፀባርቅ ነበር ያለው ዘገባው ሆኖም ዛሬ ያ አማራጭ በፖለቲካዊ እና በወታደራዊ ደረጃ የማይታሰብ ነው ብሏል።

ካይሮ 125 ሚሊዮን ሕዝብ ካላት ኢትዮጵያ ጋር ጦርነት ሊታደርግ ከቶ የማይታሰብ ነው በማለትም አሁን ግብፅ ተሸናፊ፣ ኢትዮጵያ ደግሞ አሸናፊ መሆኗን አረጋግጧል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates