አፍሪካኢትዮጵያ

የኤርትራ መንግስት የኢትዮጵያ መንግስት የሉአላዊነት ትንኮሳው ቀጥሎበታል ሲል ከሰሰ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 07/01/2018፡- የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ትላንት ባወጣው መግለጫ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት “ሉዓላዊ የባህር በር” ስለማግኘት የሚያደርጉትን ዘመቻ “ህገወጥ እና አደገኛ ዕንደራ” ሲል በይፋ አወገዘ።

ዕንደራ ማለት በትግርኛ “በደንብ ያልታሰበበት እና በስሜት የሚደረግ እንቅስቃሴ” ወይም “ውጤቱ የማያምር እና ለከንቱ ልፋት የሚዳርግ ጉዞ” እንደማለት ነው። ይህ የኤርትራ መንግስት የዛሬ የትንታኔ መግለጫ በሁለቱ የቀድሞ አጋር ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት እንደገና ውጥረት ውስጥ መግባቱን አመላካች ነው።

ትንታኔው፣ የብልጽግና ፓርቲ ባለስልጣናት የሚያራምዱት ይህ አጀንዳ “ህጋዊ ሀገራዊ ምኞት” ለማስመሰል የሚደረግ የሀሰት ትርክት ነው ብሏል።

የኤርትራ መንግስት እንደሚለው፣  የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በውጭ እርዳታ ላይ የተንጠለጠለበት እና ሀገሪቱ በከባድ የውስጥ ግጭቶች እየታመሰች ባለችበት ወቅት እንዲህ አይነት ጥያቄ ማንሳ፣  የህዝብን ትኩረት ከዋና ዋናዎቹ ችግሮች ለማስቀየስ የሚደረግ “ከንቱ መፍጨርጨር” ነው ሲል ወንጅሏል።

የኢትዮጵያ ባለስልጣናት “ወደብን በኃይልም ቢሆን” የሚለውን ንግግራቸውን እና “ታሪካዊ መብት” የሚለውን መከራከሪያቸውን የኤርትራ መንግስትባወጣው በዚህ ትንታኔው አውግዟል። ይህ አካሄድ የሉዓላዊነትን መርህ እና የአለም አቀፍ ህግን የሚጥስ ከመሆኑም በላይ፣ በቀጠናው ሰላም ላይ ከባድ አደጋ ይደቅናል ብሏል።

መግለጫው ሲያጠቃልል፣ ኤርትራ ከጎረቤቶቿ ጋር በህግና በጋራ መከባበር ላይ የተመሰረተ ትብብር ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ገልጾ፣  የኢትዮጵያን “በኃይል ያንተ ያልሆነውን የመውረስ” ስትራቴጂ ግን በፍጹም እንደማትቀበለው አስታውቋል።

ይህ ይፋዊ መግለጫ በቀጠናው የዲፕሎማሲ ምህዳር ላይ አዲስ ውጥረትን የጫረ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መንግስት የሚሰጠው ምላሽ በጉጉት ይጠበቃል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates