መካከለኛ ምስራቅ

የገልፍ ሀገራት መሪዎች የጋራ የመከላከያ ስምምነትን ለመተግበር ተስማሙ።

የዶሃው ጉባዔ እስራኤል በኳታር ላይ የሰነዘረችውን ጥቃትም አወግዟልደ

ኢትዮ ሞኒተር፡ 07/01/2018፡- የአረብ  እና ሙስሊም ሀገራት መሪዎች እስራኤል በኳተር ዶሃ ያደረሰችውን ጥቃት ተከትሎ ያካሄዱት አስቸኳይ የጋራ ስብሰባ ዛሬ ተጠናቋል።

መሪዎቹ የጋራ የመከላከያ ስምምነታቸውን ለመተግበር ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን የኳታር የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማጂድ መሀመድ አል አንሳሪ ለአልጀዚራተናግረዋል።

በተጨማሪም በጉባዔው እስራኤል በሃማስ መሪ ላይ በኳታር የሰነዘረችውን ጥቃት ሁሉም ተሳታፊዎች በማውገዝ ለኳታር ያላቸውን አጋርነት መግለጻቸው ተገልጿል።

ሀገራቱ ኳታር ለምትወስዳቸው እርምጃዎች ድጋፋችንን እንገልጻለን ያሉ ሲሆን እስራኤል ኳታርን እንደገና ኢላማ የማድረግ እድልን በተመለከተ በተደጋጋሚ የምታሰማውን ማስፈራሪያ ውድቅ አድርገዋል።

ቃል አቀባዩ “እስራኤልን በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ተጠያቂ እናደርጋለን፤ ለዚህም መሳሪያችን በአለም አቀፍ ህግጋት እና አለም አቀፍ ተቋማት ላይ ያለን እምነት ነው” ብለዋል።

የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች ባለፈው ማክሠኞ ጳጉሜ 04 ቀን የሀማስ  መሪዎችን ኢላማ ያደረገ ጥቃት መፈፀሟ የሚታወስ ሲሆን ጥቃቱም በመካከላቸው ምስራቅ ላይ ባሉ ሀገራት ስጋት አንግሶ ቆይቷል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates