መካከለኛ ምስራቅ

ግብፅ የአረብ “ኔቶ” እንዲቋቋም ሀሳብ አቀረበች፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 06/01/2018፡- የግብፁ ፕሬዝደንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ የአረብ አገራት የራሳቸውን ወታደራዊ ጥምረት እንዲያቋቁሙ የሚጠይቅ ምክረ ሀሳብ ማቅረባቸው ተገለፀ፡፡

አል አክባር የተሰኘው የሊባኖስ ጋዜጣ ባቀረበው ዘገባ ግብፅ ይህንን ምክረ ሀሳብ ያቀረበችው ‹‹በመካከለኛው ምስራቅና በአፍሪካ ቀንድ ለደህንነት ስጋት የሆኑ ጉዳዮች እየጨመሩ መጥተዋል›› በሚል ነው፡፡

የአረብ ሊግ በንግድና ኢንቨስትመንት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ተቋም መሆኑን የገለፀችው ግብፅ በመሆኑም ለተፈጠረው የደህንነት ስጋት መፍትሄ እንዲሆን ወታደራዊ ጥምረት እንዲፈጠር ጠይቃለች፡፡

ይህም እንደኔቶ አይነት ወይንም የአሜሪካ የአፍሪካ ኮማንድ ፖስት አይነት ቅርፅ እንዲኖረው ማለቷን ዘገባው አስታውቋል፡፡

ግብፅ ይህንን ሀሳብ አሁን ታንሳው እንጂ እቅዱ ከዛሬ 10 አመት በፊት በአጀንዳነት የቀረበ ነበር፡፡

በማርች ወር 2015 ማለትም የየመን እርስ በእርስ ጦርነት በተነሳበት ወቅት የአረብ አገራት የራሳቸውን ወታደራዊ ጥምረት ለመመስረት የሚያስችል ሀሳብ አቅርበው የተወያዩበት ቢሆንም በጥምር ሀይሉ ስልጣን ላይ መስማማት ሳይችሉ መቅረታቸው ይታወሳል፡፡

አሁን የግብፁ ፕሬዝደንት አጀንዳውን በድጋሚ ያቀረቡ ሲሆን በጉዳዩ ላይ በዶሀ እየተካሄደ ባለው የአረብና ሙስሊም አገራት ጉባኤ ከተገኙ መሪዎች ጋር እየተወያዩበት እንደሚገኙ ዘገባው አስታውቋል፡፡

ፕሬዝደንት አልሲሲ በዚህ እቅዳቸው 22 የአረብ አገራት የጥምረቱ አባል እንደሚሆኑ ግምታቸውን ያስቀመጡ ሲሆን እያንዳንዱ አገር ካለው ሀብት፣ ህዝብ ብዛትና ወታደራዊ አቅም በመነሳት ወታደሮችን ገንዘብ እንዲያዋጣ የሚል ሀሳብ አስፍረዋል፡፡

ለመነሻነትም በአዲሱ የአረብ ጥምር ሀይል ውስጥ ግብፅ 20 ሺ ወታደሮችን ለማዋጣት ፈቃደኛ መሆኗን መናገር ላይ መሆናቸው ተዘግቧል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates