አፍሪካ

ሱዳን ወደ መጥፋት ተቃርባለች ሲሉ የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን እየዘገቡ ነው።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 06/01/2018፡- በሰሜን ዳርፉር ግዛት ዋና ከተማ በሆነችው ኤል ፋሸር ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ላይ በተፈፀመ ከባድ ተኩስ እና ጥቃት በትንሹ 6 ንፁሀን ዜጎች ሲገደሉ በርካቶች ቆስለዋል ፣ይህም ቀደም ሲል ከተከበበች ከተማ አዲስ መፈናቀልን አስከትሏል ብሏል መረጃው።

የሰብአዊ እርዳታ ሰጪዎች አስፈላጊ አገልግሎቶች እየተበላሹ መሆናቸውን ያስጠነቀቁ የሰብአዊ መብት ተሟጓቾች ብቸኛ የሚሰራው ሆስፒታልም ሳይቀር ውሃ ማግኘት እንዳልቻለ ይገልፃሉ።

አስቸኳይ ድጋፍ ካልተደረገላቸው በጣም ተጋላጭ የሆኑት ሰዎች በቀናት ውስጥ ለከፍተኛ ረሃብ ሊጋለጡ እንደሚችሉ ያስጠነቅቃሉ።

በዳርፉር ዙሪያ፣ ሆስፒታሎች በከፍተኛ ጫና ውስጥ እንደሚገኙ የሚጠቁሙት መረጃዎቹ ባለፈው ሳምንት ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ ወደ 100 የሚጠጉ የቆሰሉ ሰዎች ወደ ህክምና መስጫ ተቋማት ገብተው የነበሩ ሲሆን በርካቶች ሲደርሱ መሞታቸዉን ድንበር የለሽ የህክምና በጎ አድራጎት ድርጅት ገልጿል።

ኤል ፋሸርን ለማምለጥ የቻሉት በሕይወት የተረፉ ሰዎች ደግሞ በከተማው ውስጥ ከአንድ አመት በላይ በፈጣን የድጋፍ ሃይሎች እና በተባባሪ ቡድኖች ተይዘው “ሊቋቋሙት የማይችሉት” ስቃይ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ድርጅቱ አስታውቋል።

በአሁኑ ሰዓት በዳርፉር በተለያዩ ቦታዎች በሱዳን ሰራዊትና በፈጣን ድጋፍ ከጪ ታጣቂዎች ከፍተኛና ተከታታይ ውጊያዎች እየተካሄዱ እንደሚገኙ ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል።

የሱዳን ሰራዊት በዳርፍ የምትገኘውን ባራ ከተማን ባለፈው ሳምንት የተቆጣጠረ ሲሆን አሁኑም የተቀሩ የዳርፉር ግዛት ቦታዎች ለማያዝ ተከታታይ ጥቃቶች እያደረገ ነው ተብሏል።

አሜሪካ፣ ግብፅ፣ የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬትስ እና ሳውዲ ዓረቢያ በሱዳን የሶስት ወራት ቶክስ አቁም ስምምነት እንዲፈፀም ቢወስኑም የሱዳኑ መሪ ጄነራል አልቡርሃን ውሳኔውን እንደማይቀበሉት አስታውቋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates