ኢትዮጵያፖለቲካ

ህወሐት “ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ከአንድ ወገን ብቻ ሊመጣ አይችልም” አለ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 05/01/2018፡- ህወሀት ትላንት ባዋጣው መግለጫ ‹‹የትግራይ ህዝብ ለሰላም ብዙ ዋጋ እየከፈለ ነው›› በማለት ጀምሮ የኢትዮጵያን መንግስት ስምምነቱን ወደጎን በመተው ከሷል፡፡

ሲቀጥልም ‹‹የኢትዮጵያ መንግስት የትግራይን ሞትና ስቃይ የሚያራዝሙ አጀንዳዎች ላይ ተጠምዷል›› ያለው ህወሀት ጨምሮም ‹‹መንግስት ወራሪ ሀይሎችን ከትግራይ ግዛት ከማስወጣት ይልቅ አሁንም እያደራጀና እያስታጠቀ ነው፡፡

እንዲሁም ከአንዳንድ ከሀዲዎች ጋር በመተባበር የታጠቁ ሀይሎችን እያደራጀና እያስታጠቀ ነው›› ሲል አስረድቷል፡፡

በተጨማሪም መንግስት ሰፊ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ እንደከፈተበት የጠቀሰው ህወሀት መግለጫውን ሲቀጥል ‹‹የትግራይ ህዝብና መሪ ድርጅቱ ህወሀት አሁንም በመርህ ላይ የተመሰረተ የሰላም እምነት አላቸው፡፡

ስለሆነም ሁሉንም ልዩነቶች በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ብቻ ለመፍታት ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ ነገር ግን ሰላም በአንድ ወገን ፍላጎት ብቻ ሊመጣ አይችልም›› ብሏል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates