አፍሪካ

የአፍሪካ ህብረት አህጉራዊ ግቦችን ለማሳካት ከተባበሩት መንግስታት ጋር እሰራለው አለ

ኢትዮ ሞኒተር፡ 05/01/2018፡- የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ የአፍሪካ ህብረት አህጉራዊ ግቦቹን ለማሳካት ከተባበሩት መንግስታት ጋር በትብብር መስራቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ባካሄደው 79ኛ ጉባኤ ላይ ከአፍሪካ ህብረት ጋር በትብብር ለመስራት ያሳለፈውን ውሳኔ አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት ሊቀመንበሩ፤ የተባበሩት መንግስታት ከአፍሪካ ህብረት ጋር ያለውን ትብብር ለማጠናከር ያሳለፈውን ውሳኔ ህብረቱ በደስታ ይቀበለዋል ብለዋል።

ውሳኔው በአፍሪካ ህብረት እና በተባበሩት መንግስታት መካከል ሰላምና እና ደህንነትን እንዲሁም ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት በትብብር ለመስራት የሚያስችል መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ከተባበርን ከአፍሪካ አልፎ ለዓለም መረጋጋት አስተዋፅኦ ማድረግ እንችላለን ያሉት ማህሙድ አሊ ዩሱፍ÷ የአፍሪካ ህብረት አህጉራዊ ግቦቹን ለማሳካት በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

በተለይም አጀንዳ 2063 እና የ2030 የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት ከተባበሩት መንግስታት ጋር በቅንጅት ለመስራት ህብረቱ ያልተቆጠበ ጥረት ያደርጋል ነው ያሉት።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates