ኢትዮጵያፖለቲካ

ትግራይ ከፌዴራል መንግስት ያላትን ግንኙነት መጥፎ ቢሆንም እንደማይቋረጥ ፕሬዝዳንት ታደሰ ወረደ ተናገሩ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 02/01/2017፡- የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ሌተና ጄኔተራል ታደሰ ወረደ አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ ከድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ጋር ሰፋ ያለ ቃለምልልስ አድርገዋል፡፡

በቃለ ምልልሳቸው ‹‹የትግራይ ህዝብ ያለፉትን አምስት አመታት ብዙ ችግሮችን አሳልፏል፡፡›› ያሉ ሲሆን አዲሱ አመት ግን የተሻለ ይሆናል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡ ጨምረውም ‹‹በ2018 የትግራይ ተጋላጭነት የሚቀንስበት፣ ውስጣዊ ችግሮቹ የሚፈቱበትና፣ ፍትህ የሰፈነበት እንዲሆን ከፍተኛ ምኞት አለኝ›› ያሉት ፕሬዝደንቱ በአዲሱ አመት ጊዜያዊ አስተዳደሩ ባለፈው አመት ያልተገበራቸውን ስራዎች እንደሚያከናውን አስታውቀዋል፡፡

ከእነዚህ መካከልም ተፈናቃዮችን ወደቤታቸው መመለስና የመሬት ጥያቄዎች እልባት እንዲያገኙ ማድረግ ላይ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡ የፕሪቶሪያ ስምምነት ፈራሚዎች ህወሀትና የፌዴራል መንግስት መሆናቸውን የጠቀሱት ሌተና ጄኔራል ታደሰ በምርጫ ቦርድ ህወሀት መሰረዙ ተፅእኖ ቢፈጥርም ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያደርጉትን ጥረት መቀጠላቸውን አስታውቀዋል፡፡

ጨምረውም ‹‹ከፌዴራል መንግስት ጋር ያለን ግንኙነት መጥፎ ወይንም ጥሩ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን መቋረጥ የለበትም፡፡ የውስጥ ችግራችን ከጊዜ ወደጊዜ የመደራደር አቅማችንን እያዳከመው በመሆኑ አንድነት ላየይ መስራት አለብን›› ያሉት ጄኔራሉ በደቡብና ትግራይ ዞን ያለውን ችግር ለመፍታት ጊዜ ወስደው መስራታቸውን አስታውቀዋል፡፡ የዞኑ ችግር ተጠንቶ የመፍትሄ እርምጃ በመቅረቡ የማስተካከያ ስራ እየተከናወነ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates