ኢትዮጵያኢኮኖሚ

የከተማ ልማት ፕሮግራም ከአንድ ሚሊዮን በላይ የስራ ዕድሎችን መፍጠሩን የዓለም ባንክ አስታወቀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 28/12/2017፡- በኢትዮጵያ የከተሞች ተቋማዊና መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም (UIIDP) እ.ኤ.አ ከ2018 እስከ 2024 ባለው ጊዜ ውስጥ ከ1.15 ሚሊዮን በላይ የስራ ዕድሎችን መፍጠሩን የዓለም ባንክ አስታወቀ።

ከእነዚህ ውስጥ 915,000 የሚሆኑት የጊዜያዊ፣ 237,000 የሚሆኑት ደግሞ ቋሚ የስራ መደቦች ናቸው ብሏል።

ባንኩ አዲስ ባወጣው ሪፖርት፤ የኢትዮጵያ የከተማ ነዋሪ ቁጥር እ ኤ አ ከ2012 ከነበረው 15 ሚሊዮን ወደ 42 ሚሊዮን ሊጠጋ እንደሚችል ገልፆ፤ ይህም በመሰረተ ልማት፣ በአገልግሎት አቅርቦትና በስራ ዕድል ላይ ተግዳሮት ሊፈጥር እንደሚችል አመልክቷል።

የከተሞች ተቋማዊና መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም፤ የተቋማትን አቅም ለማጠናከርና በመሰረተ ልማት  አማካኝነት የስራ ዕድል ለመፍጠር በሀገሪቱ ባሉ 117 ከተሞች ተግባራዊ ተደርጓል ተብሏል።

እንደ ዓለም ባንክ ሪፖርት፣ ፕሮግራሙ የከተማ አስተዳደሮች ተቋማዊ ግንባታ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።

በዚህም ምክንያት፣ ጠንካራ የፋይናንስ አስተዳደር ሥርዓቶችን በመዘርጋት፣ የአስተዳደር ሂደቶችን በማሻሻል እና በጊዜው ኦዲት በማድረግ፣ ከተሞች በራሳቸው እድገት ላይ ቁጥጥር እንዲኖራቸው አስችሏል ብሏል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates