የተለያዩ

በምስራቃዊው የስደት መስመር ህይወታቸው የሚያልፍ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ቢሆንም የፍልሰተኞች እንቅስቃሴ አለመቀነሱ ተመላከተ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 28/12/2017፡- አደገኛ በሆነውና የአፍሪካ ቀንድን ከአረብ ባሕረ ገብ መሬት ጋር በሚያገናኘው ምስራቃዊ የፍልሰት መስመር ላይ የሚሞቱና የሚጠፉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ቢሆንም፣ የስደተኞች እንቅስቃሴ አለመቀነሱን የተባበሩት መንግስታት የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) አስታወቀ።

ድርጅቱ ባወጣው ሪፖርት መሠረት፣ ከጥር እስከ ሰኔ 2025 ባለው ጊዜ ውስጥ ከዚህ መስመር የተሰደዱ ስደተኞች ቁጥር አንድ ሶስተኛ (በ34 በመቶ) የጨመረ ሲሆን ይህም በ2024 በተመሳሳይ ጊዜ ከነበረው 178,300 ወደ 238,000 ከፍ ብሏል። በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ የሞቱ ወይም የጠፉ ስደተኞች ቁጥር በ2024 ከነበረው 310 ወደ 348 ከፍ ማለቱም ተመላክቷል።

ከነዚህ ውስጥ፣ በሁለተኛው ሩብ ዓመት ብቻ 78 ሰዎች የሞቱ ወይም የጠፉ ሲሆን፣ አብዛኛዎቹ የሞቱት በጅቡቲ ኦቦክ በረሃ ውስጥ ነው። ስደተኞቹ በጀልባ መስመጥ አደጋ እንደሚሞቱ፣ በየመን በሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ተኩስ እንደሚገደሉ እና በሰሜን ሶማሊያ ዝርፊያ እንደሚፈጸምባቸው ሪፖርቱ ጠቁሟል።

Show More

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates