“ሺ ጂንፒንግ፡ የሰብአዊ መብቶችን መከበርና መጠበቅ” በሚል ርእስ ነተፃፈው መፅሐፍ ላይ የአንባቢያን መድረክ በኢትዮጵያ ተካሄደ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 22/12/2017፡- የቻይና የሰብአዊ መብት ጥናት ማህበር ስራ አስፈፃሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ጂያንግ ጂያንጉዎ መፅሃፉ በ13 የውጪ ቋንቋዎች ታትሞ በአለም አቀፍ ደረጃ አንባቢዎችን በሰብአዊ መብት፣ በፖለቲካ፣ በአካዳሚክ ጥናትና ምርምር፣ በመገናኛ ብዙሃን እና በቲንክ ታንኮች በመሳብ የተዘጋጀ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ከዚህ መፅሃፍ አንባቢዎች ሺ እንደ ትልቅ ፓርቲ መሪ እና እንደ ትልቅ ሀገር ያላቸውን ራዕይ ለአለም ማሳየት እንደሚችሉ የቻይና ህዝቦች ፖለቲካል ምክር ቤት ብሄራዊ ኮሚቴ አባል እና የሲፒሲሲ ብሔራዊ ኮሚቴ እንዲሁም የብሄር እና ሀይማኖት ጉዳዮች ኮሚቴ ምክትል ዳይሬክተር ጂያንግ ተናግረዋል።
የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ለዘመናት የዘለቀው የሰብአዊ መብቶችን በማክበር እና በመጠበቅ ላይ ያለውን ቁርጠኝነት እና ቻይና የሰብአዊ መብቶችን በማሳደግ ረገድ የተከተለችውን ገለልተኛ መንገድ አንባቢዎች ግንዛቤ ማግኘት ይችላሉ ያሉት ጂያንግ መፅሃፉ ለአፍሪካ ሀገራት ዘመናዊነትን ለማራመድ፣ የሰብአዊ መብት አስተዳደርን እና የህዝብን ደህንነት ለማሻሻል ጠቃሚ ማጣቀሻዎችን እንደሚሰጥ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼን ሃይ ባደረጉት ንግግር ቻይና እና አፍሪካ ህዝቦችን ያማከለ አካሄድ እና ከሀገራዊ ሁኔታዎች ጋር የሚስማማ የሰብአዊ መብት ጎዳና ላይ ያተኩራሉ ሲሉ የሰብአዊ መብት ጉዳዮችን ፖለቲካዊ ማድረግን ግን ይቃወማሉ ብለዋል።
ቻይና እና ኢትዮጵያ በቻይና አፍሪካ የሰብአዊ መብት ልውውጦችና ትብብር ውስጥ አርአያነት ያለው ሚና የተጫወቱ ሲሆን፥ በቻይና አፍሪካ የሰብአዊ መብት ልውውጦች እና ትብብር በቻይና እና በአፍሪካ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥያቄ ከማስቀደም ባለፈ የቻይና-አፍሪካ ማህበረሰብ የወደፊት የጋራ ተጠቃሚ እንዲሆን እና የሰብአዊነትን እድገት ለማስተዋወቅ አስተዋፅዖ ይኖረዋል ብለዋል።
የላይቤሪያ የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚንስትር ጄዲ ሞውብራይ አርማህ በበኩላቸው እያንዳንዱ ሀገር ከራሱ ታሪክ፣ ባህልና የዕድገት ደረጃ በመነሳት አገራዊ ነባራዊ ሁኔታውን የሚያስማማ መንገድ በመቅረጽ፣ የጋራ ክብርን፣ ፍትህና እኩልነትን ማስከበር እንዳለበት አሳስበዋል።
በዝግጅቱ ላይ 150 የሚጠጉ የአፍሪካ የፖለቲካ፣ የአካዳሚክ፣ የመገናኛ ብዙሃን እና የተማሪ ማህበረሰቦች ተወካዮች ተገኝተዋል።