የሱዳን የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር በ1.65 ሚሊዮን ቀንሷል ሲል ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አስታወቀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 22/12/2017፡- የሱዳን የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ከፍተኛ ቁጥር ደርሶበት ከነበረው ጥር ወር በኃላ ወደ 1.65 ሚሊዮን የሚጠጋ ቀንሷል ሲል የመንግስታቱ ድርጅት አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ባወጣው አዲስ ሪፖርት አመልክቷል።
ይህ የሆነው በዋነኛነት ወደ ቤታቸው የሚመለሱ ሰዎች በመጨመሩ ነው ብሏል።
እ.ኤ.አ. ከሚያዝያ 2025 መጨረሻ ጀምሮ በሱዳን 18ቱ ግዛቶች 9,937,444 ሰዎች ተፈናቅለዋል። ይህ አሃዝ በጥር 2025 ከተመዘገበው ከፍተኛው የተፈናቃይ ህዝብ ቁጥር 11.5 ሚሊዮን ከፍተኛ ቅናሽ ማሳየቱ ገልጿል።
በተፈናቀሉ ህዝቦቻቸው ላይ ከፍተኛ አንጻራዊ ቅናሽ ያጋጠማቸው ክልሎች ካሳላ (20 በመቶ ቅናሽ)፣ ቀይ ባህር (14 በመቶ ቅናሽ) እና ወንዝ አባይ (11 በመቶ ቅናሽ) ናቸው። በነዚህ ምስራቃዊ ግዛቶች የተስተናገዱት አብዛኞቹ ተፈናቃዮች በካርቱም፣ አልጃዚራህ፣ ሴናር እና ሌሎች ግዛቶች ወደ መጡበት አካባቢ እየተመለሱ ነው።
የአገር ውስጥ መፈናቀል ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱን ተከትሎ እየተካሄደ ያለው ግጭት በተለይ በዳርፉር ክልል ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው እንዲፈናቀሉ ማድረጉን ቀጥሏል። በሰሜን ዳርፉር በአል ፋሸር በተከሰተው ግጭት ተደጋጋሚ መፈናቀልን አስከትሏል፣ብዙ ተፈናቃዮች ወደ ሌሎች የዳርፉር ግዛቶች ተዛውረዋል።
ግጭቱ ከሚያዝያ 2023 ጀምሮ ከ7.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች አዲስ ተፈናቅለዋል። ለተፈናቃዮች ከፍተኛው የትውልድ ግዛቶች ካርቱም (31%)፣ ደቡብ ዳርፉር (21%) እና ሰሜን ዳርፉር (20%) ናቸው። ከተፈናቀሉ ቤተሰቦች ውስጥ ግማሽ ያህሉ (47%) የሚኖሩት ከቤተሰቦቻቸው እንደሆነ መረጃው አሳይቷል።
ከጥር 2024 ጀምሮ በግምት 272,361 ሰዎች ከግብፅ ወደ ሱዳን መመለሳቸው ተዘግቧል። ሆኖም ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በአጠቃላይ ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሱዳንን ጥለው ወደ ጎረቤት ሀገራት ማለትም ግብፅ፣ ቻድ እና ደቡብ ሱዳን መሰደዳቸው መረጃው ያሳያል።