መካከለኛ ምስራቅ

እስራኤል በሆስፒታል ላይ በፈጸመችው ጥቃቶች አምስት ጋዜጠኞችን ጨምሮ 20 ሰዎች ተገደሉ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 20/12/2017፡- እስራኤል በኻን ዩኒስ ከተማ ናስር ሆስፒታል በተከታታይ ሁለት ጊዜ በፈጸመችው ጥቃት ለአለም አቀፍ ሚዲያዎች የሚሰሩ አምስት ጋዜጠኞችን ጨምሮ 20 ፍልስጤማውያን መገደላቸውን በሐማስ ስር ያለው የጋዛ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ጋዜጠኞቹ ለሮይተርስ፣ አሶሺዬትድ ፕሬስ፣ አልጀዚራ እና ዘ ሚድል ኢስት አይ ጋር ይሰሩ እንደነበር ሚዲያዎቹ አረጋግጠዋል።

በዚህ ጥቃት አራት የጤና ባለሙያዎች መገደላቸውን የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ተናግረዋል።

በመጀመሪያው ጥቃት የተጎዱ ሰዎችን እያገዙ የነበሩ ሰዎች በድጋሚ በተፈጸመ ጥቃት መመታቸውን ከአካባቢው የወጡ ቪዲዮዎች ያሳያሉ።

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ በሆሰፒታሉ ላይ የተፈጸመውን ጣምራ ጥቃት “አሳዛኝ ጥፋት” ሲሉ የገለጹት ሲሆን ወታደራዊ ባለስልጣናት “ምርመራ እያከናወኑ ነው” ብለዋል።

እስራኤል በጋዛ ላይ የተቀናጀ ጥቃት ከጀመረች መስከረም 26/ 2016 ዓ.ም ጀምሮ የተገደሉ ጋዜጠኞች 200 ገደማ አድርሷቸዋል።

የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪው ሲፒጄ ቢያንስ 178 ፍልስጤማውያን ጋዜጠኞች በእስራኤል መገደላቸውን አስታውቆ ነበር።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates