ማህበራዊኢትዮጵያ

ከ290 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ 3ቱ ብቻ ፈቃዳቸው እንደፀና ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 20/12/2017፡- በዳግም ምዝገባ ከተመዘገቡ 290 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ሶስቱ ብቻ መስፈርቱን አሟልተዋል አለ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን።

በባለስልጣኑ የተቋማት ፈቃድ አሰጣጥ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሕይወት አሰፋ እንዳሉት÷ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ለመመዝገብ በተዘጋጀው አዲሱ የዳግም ምዝገባ መገምገሚያ መስፈርት 375 ተቋማትን ለመመዝገብ ታቅዶ 290 ተቋማት ተመዝግበዋል፡፡

290 ተቋማት ተመዝግበው በተካሄደው የመጀመሪያ ዙር ግምገማ መስፈርቱን ያሟላ ተቋም ባለመኖሩ መስፈርቱ ተሻሽሎ ሁለተኛ ዙር ግምገማ መካሄዱን አንስተዋል፡፡

መንግስት ተቋማቱ ራሳቸውን አብቅተው በትምህርት ሥርዓቱ እንዲቀጥሉ በማሰብ 3ኛ ዙር መስፈርቱን በማሻሻል ዝቅተኛውን መስፈርት እንዲያሟሉ ዕድል መሰጠቱንም አስታውሰዋል፡፡

በዚህም 3 ተቋማት ፤ በ3 ካምፓስ በ17 የትምህርት መስክ ዝቅተኛውን መስፈርት አሟልተው ፈቃዳቸው መጽናቱን ተናግረዋል።

በ12 ወራት ማሟላት የሚጠበቅባቸውን እንዲያሟሉ ቅድመ ሁኔታ የተሰጣቸው ደግሞ 25 ተቋማት ፤ በ37 ካምፓስ በ146 የትምህርት መስክ የተገጓደሉትን እንዲያሟሉ መደረጉን አስረድተዋል።

በሌላ በኩል በ6 ወራት እንዲያሟሉ ውሳኔ የተላለፈባቸው ተቋማት መኖራቸውን ጠቁመው ÷ 85 ተቋማት ቀርበው መመዝገብ ባለመቻላቸው በራሳቸው ጊዜ ከሥርዓቱ መውጣታቸውን አመልክተዋል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates