አፍሪካ

የመጀመሪያው ወደ አፍሪካ ሕብረት የድጋፍ ተልዕኮ በሶማሊያ የሚቀላቀሉት የግብፅ ወታደሮች ስልጠና ማጠናቀቃቸው ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 20/12/2017፡- የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስቴር ለግብፅ ጦር ሃይሎች የመጀመሪያ የስልጠና መርሃ ግብር መጠናቀቁን ተከትሎ የግብፅ ወታደሮችን በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ (AUSSOM) ውስጥ ማሰማራቱን ተገልጿል።

“ግብፅ የሶማሊያን ደህንነት ለመደገፍ እና የሶማሊያ ብሄራዊ ጦርን አቅም ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያጎላ ነው” ብሏል መረጃው።

የግብፅ ወታደር ወደ አፍሪካ ሕብረት ሰላም አስከባሪ መቀላቀል በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል በተፈጠረ ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት ምክንያት የመጣ ሲሆን ይህም ኢትዮጵያ በጥር 2024 ከሶማሌላንድ ጋር ባደረገችው የመግባቢያ ስምምነት ተከትሎ የተከሰተ መሆኑን ይታወቃል።

ሞቃዲሾ ኢትዮጵያ በአዲሱ የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ ውስጥ መሳተፍን መጀመሪያ ላይ ብትቃወምም፣ በኋላም ሁለቱም ወገኖች በAUSSOM ስር እንዲቆዩ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates