አውሮፓ

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ በኖርዌይ ፅንፈኛ ወጣት መገደሏን ተከትሎ ቁጣን ቀሰቀሰ። 

ኢትዮ ሞኒተር፡ 20/12/2017፡- ባሳለፍነው እሁድ ነሐሴ 18/ 2017 ዓ/ም የኖርዌይ ዜግነት ያላት የ34 ዓመቷ የኦሮሞ ተወለጅ ተሚማ ንብራስ ጁሃር በኦስሎ ከተማ መገደሏ ተገለጸ።

ተሚማ የተገደለችው በኦስሎ ከተማ በምትሰራበት “ጄምት” (Gemt) ተብሎ በሚጠራ የህፃናት ተራዕዶ ድርጅት ውስጥ መሆኑ ተዘግቧል።

ፖሊስ በተሚማ ግድያ የተጠረጠረ የ18 አመት ወጣት በቁጥጥር ስር ማዋሉን ባለስልጣናት የገለጹ ሲሆን፤ ግለሰቡ በፖለቲካዊ ጥላቻ ወንጀሉን እንደፈፀመ መናገሩን እና የፅንፈኝነት ንግግሮችን ማድረጉን ገልጸዋል።

ዐቃቤ ሕግ ተጠርጣሪው ትውልደ ኢትዮጵያዊት የሆነችውን የኖርዌይ ዜጋ ግድያን ጨምሮ በሽብርተኝነት ወንጀሎች ክስ እንደቀረበበት አስታውቋል።

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት የአምነስቲ ኢንተርናሽናል፤ ተሚማ በህጻናት ተራዕዶ ስራ ላይ ሳለች መገደሏን “አሰቃቂ ድርጊት” ሲል ግድያውን በጽኑ አውግዟል።

የኖርዌይ መንግስት የግድያውን መንስኤ ብቻ ሳይሆን፣ ይህ አሰቃቂ ድርጊት እንዴት ሊፈጸም እንደቻለ ጥልቅ ምርመራ እንዲያደርግም ጠይቀዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates