አፍሪካ

የአፍሪካ የደህንነት እና የስለላ አገልግሎት ኮንፈረንስ በሊቢያ ቤንጋዚ ከተማ ዛሬ ተጀመረ።

የኮንፈረንሱ ዋና ዓላማ በአፍሪካ ሰላም እና ልማት ላይ ለመወያየት ነው።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 19/12/2017፡- ዛሬ በቤንጋዚ በተጀመረው 20ኛው የአፍሪካ የደህንነትና ስለላ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ሊብያ ከጋቦን ፕሬዝዳንትነት ተረክባለች።

የመሪዎቹ ስብሰባ ከመጀመሩ በፊት ለሶስት ቀናት የባለሞያዎች ውይይት የተካሄደ ሲሆን ቅዳሜ ነሐሴ 17 ቀን 2017 ዓ/ም መጠናቀቁ ይታወሳል።

በአህጉሪቱ የጸጥታ ጉዳዮችን እና በአባል ሀገራቱ መካከል ያለውን የማስተባበር ዘዴን የተመለከተ የሶስት ቀናት የውይይት መድረክ እና ምክክር ተከትሎ የአፍሪካ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት የባለሞያዎች ኮሚቴ ስራ ቅዳሜ ተጠናቋል።

የኮሚቴው ግኝቶች እና የውሳኔ ሃሳቦች ከዛሬ ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሁለት ቀናት በሚካሄደው የአፍሪካ የስለላ ሃላፊዎች ይፋዊ ስብሰባ ላይ ለውይይት ቀርቦ እንዲፀድቅ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ስብሰባው ከ51 ሀገራት የተውጣጡ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን እና ቀጠናዊ እና አለምአቀፍ አካላት የሚሳተፉበት ይሆናል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates