አፍሪካ
የሱዳኑ ፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሐይል በኤል ፋሸር ውስጥ በአዲስ ጭካኔ እና የዘር ማጽዳት ወንጀል ተከስቷል ተባለ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 19/12/2017፡- የተከበበችውን የሰሜን ዳርፉር ዋና ከተማ ኤል ፋሸርን ለመሸሽ በሚሞክሩ ሰላማዊ ሰዎች ላይ አዲስ የግድያ፣ አፈና እና ብሔርን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን መፈፀሙን ተገልጿል።
ታጣቂ ሐይሉ በከተማዋ እና በአቡ ሹክ ካምፕ 190,000 ተፈናቃዮችን በሚጠለልበት ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት ተባብሷል ተብሏል።
የካምፑ ቃል አቀባይ ለሱዳን ትሪቡን እንደተናገሩት ታጣቂ ሐይሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን በግዳጅ እያፈናቀለ ነው።
ዘገባው እነደሚያመላክተው የተወሰኑት ወደ ኤል ፋሸር እንዲመለሱ ሲደረግ፣ ሌሎች ደግሞ በአብደል ዋሂድ ኑር የሚመራው የሱዳን ነፃ አውጪ ንቅናቄ ወደተቆጣጠራቸው አካባቢዎች መሰደዳቸውን ተገልጿል።
በ RSF ታፍነው የተወሰዱት ሲቪሎች ቁጥር ከ20 በላይ ሆኗል ያሉት ቃል አቀባዩ “ሠራዊቱን እየደገፉ ነው በሚል ሰበብ ሊገደሉ ይችላሉ” ሲሉም ተናግረዋል።
ጥቃቶቹ ከሚያዝያ 2024 ጀምሮ የተከበበችውን ከተማዋን ለመቆጣጠር ቡድኑ የጀመረውን አዲስ ግፊት አካል ሲሆን ይህም ሰብአዊ እርዳታን በመዝጋት ከፍተኛ የሆነ የረሃብ ቀውስ አስከትሏል።
የሱዳን ዶክተሮች ኔትዎርክ መግለጫ እንደሚለው RSF ከጥቃት ለማምለጥ ሲሞክሩ አምስት ህጻናትን ጨምሮ 13 ሰዎችን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏል።