አፍሪካ
ጃፓን ህንድ ውቅያኖስን ከአፍሪካ ጋር የሚያገናኝ ‘የኢኮኖሚ ዞን’ ሀሳብ አቀረበች።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 15/12/2017፡- የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሽገሩ ኢሺባ ህንድ ውቅያኖስን ከአፍሪካ ጋር የሚያገናኘው የኢኮኖሚ ዞን ለመፍጠር ፍላጎት እንዳላት አስታውቋል።
አገሪቷ በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ትልቅ ሚና ለመጫወት የፈለገችው የአሜሪካ በዚያ መገኘት እየቀነሰ እና የቻይና ተጽእኖ በፍጥነት እያደገ ባለበት ወቅት ነው።
ኢሺባ የቶኪዮውን ዓለም አቀፍ የአፍሪካ ልማት ኮንፈረንስ (ቲካድ) በጀመረበት ወቅት እንደተናገሩት የህንድ ውቅያኖስ ከአፍሪካ አህጉር ጋር በማገናኘት በቀጠናው ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ለማጠናከር እና ነፃ ንግድን ለማስተዋወቅ ቃል ገብቷል።
ኢሺባ “ጃፓን በአፍሪካ የወደፊት ተስፋ ታምናለች” ያሉ ሲሆን “ጃፓን የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ አካባቢ ጽንሰ-ሀሳብ ትደግፋለች” ይህም የቀጠናውን ተወዳዳሪነት ለማጠናከር ያለመ ነው” ብሏል።
በዘንድሮው እየተካሄደ ያለውን የቲካድ ኮንፈረንስ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የታሪፍ ጭማሪ እና የውጭ ዕርዳታ መርሃ ግብሮች ከፍተኛ ቅነሳ በአፍሪካ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ ባለበት ወቅት ነው።