በሱዳን እየተባባሰ የመጣውን ቀውስ እንዳሳሰበው በአሜሪካ የሚመራው የሸምጋዮች ቡድን ገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 15/12/2017፡- በአሜሪካ የሚመራ የሽምግልና ቡድን “በሱዳን ያለው ቀጣይነት ያለው የሰብአዊ ሁኔታ መባባስ የሚያሳዝን ነው” በማለት ተፋላሚ ወገኖች ሲቪሎችን ለመጠበቅ እና ዕርዳታ እንዲደርስ መፍቀድ እንዳለባቸው አሳስቧል።
አሜሪካ፣ ግብፅ ፣ ሳዑዲ አረቢያ ፣ ስዊዘርላንድ ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ፣ የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያካተተው የሰላም ቡድን “በከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እና ረሃብ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን እና በቁልፍ አካባቢዎች ተደራሽነትን የሚያዘገዩ እንቅፋቶችን” እንዳሉ ጠቅሷል።
“ሲቪሎች ለዚህ ጦርነት ከፍተኛውን ዋጋ መክፈላቸውን ቀጥለዋል” ያለው ቡድኑ በሰጠው መግለጫ የሰብአዊ ፍላጎቶች “አስጨናቂ ደረጃ ላይ መድረሱን” አፅንዖት ሰጥቷል።
ቡድኑ በግጭቱ ውስጥ ያሉ አካላት የቢሮክራሲያዊ እንቅፋቶችን እንዲያነሱ፣ የአቅርቦት መስመሮችን እንዲጠብቁ፣ ቴሌኮሙኒኬሽን እንዲታደስ እና እ.ኤ.አ. በግንቦት 2023 የተፈረመው የጅዳ ስምምነት በሱዳን ጦር ሃይሎች እና በፈጣን ድጋፍ ሃይሎች መካከል ያሉ ግጭቶችን ለማስቆም ያለመ እንደነበር አስታውሷል።
የሱዳን ጦር እና ፈጣን ድጋፍ ሐይሉ መካከል ሚያዝያ 2023 የተጀመረው ጦርነት ከ20,000 በላይ ዜጎች እንደቀጠፈ እና 14 ሚሊዮን የሚገመቱት ከቀያቸው እንዳፈናቀለ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል።