መካከለኛ ምስራቅ

እስራኤል የጋዛን ህዝብ ለማስራብ በፖሊሲ ደረጃ እየሰራች ነው ሲል አሚኒስቲ ኢንተርናሽናል ከሰሰ።

ኢትዮ ሞኒተር፡12/12/2017፡- እስራኤል በተከበበችው የጋዛ ሰርጥ “ሆን ተብሎ የረሃብ ዘመቻ” እያካሄደች ነው ሲል የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቋል።

በፍልስጤም ግዛት ከተመጣጠነ ምግብ እጥረት ጋር በተያያዙ ምክንያቶች ሰባት ተጨማሪ ሰዎች መሞታቸውን የአካባቢው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እሁድ ዕለት ማስታወቁ ይታወሳል።

የመብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል እስራኤል “ሆን ብላ  የረሃብ  ፖሊሲ” አውጥታለች ሲል ወንጅሏል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የእርዳታ ድርጅቶች በፍልስጤም ግዛት ውስጥ ረሃብ እንዳለ ሲያስጠነቅቁ መቆየታቸው ይታወሳል።

በጋዛ ሰርጥ የሚፈቅደውን እርዳታ በእጅጉ የምትገድበው እስራኤል ለ22 ወራት በዘለቀው ጦርነት “ረሃብን እንደጦር መሳሪያ እየተጠቀመች ነው” የሚለውን ክስ ውድቅ አድርገዋለች።

አምነስቲ የተፈናቀሉ ፍልስጤማውያን እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ያለባቸውን ህጻናት ህክምና ያደረጉ የህክምና ባለሙያዎችን ምስክርነት ጠቅሶ ባወጣው ዘገባ ግን “እስራኤል በተያዘችው ጋዛ ሰርጥ ሆን ተብሎ የረሃብ ዘመቻ እያካሄደች ነው” ብሏል።

ቡድኑ እስራኤልን “የፍልስጤም ህይወት ጤናን፣ ደህንነትን እና ማህበራዊ መዋቅርን ስልታዊ በሆነ መንገድ ታጠፋለች” ሲል ከሰዋል።

“እስራኤል በጋዛ ውስጥ ባሉ ፍልስጤማውያን አካላዊ ውድመትን ለማምጣት በማሰብ ባለፉት 22 ወራት ሆን ብላ የነደፈችው እና የተገበረችው የእቅዶች እና የፖሊሲዎች ውጤት ነው ያለው መግለጫው ይህም እስራኤል በጋዛ ፍልስጤማውያን ላይ እየፈጸመችው ያለውን የዘር ማጥፋት መንጀል አካል ነው” ሲል አምነስቲ ኣጋልጣል።

በሚያዝያ ወር እስራኤል በፍልስጤማውያን ላይ ጋዛውያንን በግዳጅ በማፈናቀል እና በተከበበችው ግዛት ላይ ሰብአዊ እልቂት በመፍጠር “በቀጥታ የዘር ማጥፋት ወንጀል” ፈጽማለች ሲል አሚኒስት ከሷል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates