የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሐይል በሱዳን ትይዩ መንግስት ለመመስረት ማቀዱን ውድቅ አደረገ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 08/12/2017፡ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት የሱዳን ፓራሚሊታሪ ቡድን በሚቆጣጠራቸው አካባቢዎች ተቀናቃኝ መንግስት ለመመስረት ያቀደውን እቅድ ውድቅ በማድረግ እርምጃው የሀገሪቱን የግዛት አንድነት አደጋ ላይ እንደሚጥል እና የእርስ በርስ ጦርነትን የበለጠ ሊያባብሰው እንደሚችል አስጠንቅቋል።
የተባበሩት መንግስታት ለሱዳን ሉዓላዊነት፣ ነፃነት እና አንድነት ያለውን የማያወላውል ቁርጠኝነት በማያሻማ መልኩ አረጋግጧል ተብሏል።
ሱዳንን ለማዳከም የሚወሰዱ እርምጃዎች የሱዳንን የወደፊት እጣ ፈንታ ብቻ ሳይሆን ሰፊውን የቀጠናው አካባቢ ሰላምና መረጋጋት አደጋ ላይ ይጥላሉ ሲል መግለጫው አስጠንቅቋል።
15 አባላት ያሉት ምክር ቤቱ እንደገለፀው የፈጣን ድጋፍ ሃይሎች መግለጫ “አገሪቷን የሚበታተን እና ቀድሞው የነበረው የከፋ ሰብአዊ ሁኔታን የሚያባብስ ነው” ብሏል።
የፀጥታው ምክር ቤት በሰላማዊ መንገድ ወደ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ብሄራዊ መንግስት የሚመራ ሽግግር ጀምሮ ዘላቂ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ እና ጦርነቱን ፖለቲካዊ እልባት ለመስጠት ሁኔታዎችን ለመፍጠር ሁለቱ ወገኖች የሚያደርጉትን ውይይት እንደገና መጀመር ነው ሲል በድጋሚ ገልጿል።
የምክር ቤቱ አባላት “ረሃብ እና ከፍተኛ የምግብ ዋስትና እጦት የመስፋፋት አደጋ በተጋረጠበት” ኤል-ፋሸር ታጣቂ ቡድኑ ከበባ እንዲያነሳ ባለፈው አመት ያፀደቁትን ውሳኔ አስታውሰዋል።
በተከበበችው ከተማ ላይ የአርኤስኤፍ ጥቃት እንደገና መጀመሩን በመግለጽ “በጣም ያሳስባል” ብለዋል።