አፍሪካ

በሞቃዲሾ አቅራቢያ ከባድ ግጭት መቀስቀሱ ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 08/12/2017፡ ሞቃዲሾ ውስጥ ከአፍሪካ መንደር አካባቢ እስከ ታራብዩንካ ድረስ ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ መሰማቱን ነዋሪዎች ገለፁ።

ግጭቱ የተቀሰቀሰው ለፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ታማኝ በሆኑ ሃይሎች እና ቤታቸውን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ባለመሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል መሆኑን የአካባቢው ምንጮች ይገልጻሉ።

አከራካሪው መሬት – በታራብካን የሚገኘውን የቀድሞ የHorsed ወታደራዊ ካምፕን ጨምሮ – ለህዝብ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ለአደን ማዶ መሰጠቱን ተከትሎ ነው ግጭቱ የተቀሰቀሰው።

ሶማሊያ ላለፉት ሶስት ዓስርት ዓመታት ከግጭትና ፖለቲካዊ ቀውስ ልትወጣ አልቻለችም።

በአሁኑ ወቅት ከአልቃይዳ ግንኙነት እንዳለው የሚነገርለት የአልሸባብ የሽብር ቡድን አብዛኛውን የገጠር አከባቢ እንደተቆጣጠረው ይገለፃል።

ከዚህ በተጨማሪ አልሸባብ ከዋና ከተሟ ሞቋድሾ በቅርብ ርቀት በሚገኙ ከተሞችም በየቀኑ ጦርነት እያካሄደ እንደሚገኝ ይገለፃል።

የራስ ገዠ የሆኑት የሶማሊላንድ፣ ጁባላንድና ፑንትላንድ አስተዳደሮችም ለማእከላዊው መንግስት የሚታዘዙ ኣይደለም።

ሰሙኑን ኢትዮጵያን በምታዋስነው ጌድኦ ግዛት በጁባላንድ እና ሶማሊያ መንግስት ሰራዊት የተደረገ ጦርነትም የዚህ ማሳያ እንደሆነ ይገለፃል።

እንዲሁም በአሁን ጊዜ ሶማሊያ እንደነ ግብፅ፣ ቱርክ፣ ኢሚሬትስና አሜሪካ ያሉት የውጭ ሐይሎች መፈንጫ ሆና እንደምትገኝ መረጃዎች ያሳያሉ።

ይህ ደግሞ ለአፍሪካ ቀንድ ደህንነት ከፍተኛ ስጋት እየፈጠረ መጥቷል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates